የቻይና አራት ከተሞችም በርካታ ቢሊየነሮች የሚኖሩባቸው ተብለው እስከ10ኛ ባለው ደረጃ ተካተዋል
በአለማችን በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ሃብት ያካበቱ 2 ሺህ 640 ቢሊየነሮች በፎርብስ የ2023 የባለጠጎች ዝርዝር ሰፍረዋል።
ከዚህ ውስጥ 735ቱ በአሜሪካ የሚኖሩ ናቸው።
ግዙፏ የንግድ ከተማ ኒውዮርክም በቤጂንግ በ2021 እስክትነጠቅ ድረስ ለሰባት ተከታታይ አመታት ቀዳሚዋ የቢሊየነሮች ከተማ እንደነበረች የፎርብስ መረጃ ያወሳል።
ከ2022 ጀምሮ ቀዳሚነቷን ዳግም የተቆጣጠረችው ኒውዮርክ 101 ቢሊየነሮች ይኖሩባታል።
በከተማዋ የሚገኙ ቢሊየነሮች ጠቅላላ ሃብት ቢደመር 616 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።
ቻይናም ቤጂንግን ጨምሮ አራት ከተሞቿን በርካታ ቢሊየነሮች በሚኖሩባቸው 10 የአለማችን ከተሞች ዝርዝር ውስጥ ማካተት ችላለች።
በርካታ ቢሊየነሮች የሚኖሩባቸውን ከተሞች ዝርዝር ይመልከቱ፦