ጣልያን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ዴንማርክ በወጣት ቢሊየነሮች ቁጥር ቀዳሚ ሆነዋል
10 የዓለማችን ወጣት ቢሊየነሮች
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጎድቶ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ በማገገም ላይ ቢሆንም የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት መከሰት ኢኮኖሚው ቶሎ እንዳያገግም አድርጎታል።
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነትን ተከትሎ የቀይ ባህር ትራንስፖርት ቀውስ መከሰት ተጨማሪ የኢኮኖሚ ስጋትም ሆኗል።
ይህ በዚህ እንዳለ ፎርብስ እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ የወጣት ቢሊየኖርችን ሀብት ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የጣልያኖቹ እህት እና ወንድማማቾች እያንዳንዳቸው አራት ቢሊዮን ዶላር ሀብት በመያዝ ቀዳሚ ተብለዋል።
ሌላኞቹ ደቡብ ኮሪያዊያን ወጣት ወንድማማቾች ኪም ጆንግ ዩን እና ኪም ጆንግ ሚን እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ሀብት አላቸው።
ሌላኛው የዓለማችን ወጣት ቢሊየነር ዴንማርካዊ ሲሆን የሀብት መጠኑ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ሀብት እንዳለው ተገልጿል።