የአየር ንብረትን መላመድ፡ ከወፎች ምን እንማራለን?
የአክርቲክ የባህር ወፎች የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን አደጋ መቋቋም እንደሚችሉ ጥናት አመልክቷል
በአኗኗራቸው ወፎቹ ምክንያት ተጽዕኖውን ሊቋቋሙት ይችላሉ ብለዋል
የአክርቲክ የባህር (ጥቁርና ነጭ) ወፎች የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለውን አደጋ መቋቋም እንደሚችሉ አዲስ ጥናት አመልክቷል።
በምድር ሰሜናዊ ክፍል የሚራቡት ወፎቹ፤ በከፊል-ቋሚ የሆነ መኖሪያ አላቸው። በጋውን ለማሳለፍ ወደ አንታርክቲካ ይበራሉ።
በህይወታቸው ዘመናቸው የሚያደርጉ ጉዞ፤ ጨረቃን ሦስት ጊዜ መጓዝ ማለት ነው።
በብሪታንያ የኤክስተር ዩኒቨርሲቲ እና ሜት ቢሮ መሪነት ተመራማሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ በአርክቲክ ወፎች ላይ የሚችለውን ተጽዕኖ ፈትሸዋል።
ተመራማሪዎቹ የአየር ንብረት ለውጥ በአጠቃላይ በስደተኛ የባህር ወፎች ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ቀላል ነው በማለት ደምድመዋል።
በእነዚህ አካባቢዎች በአኗኗራቸው ምክንያት ተጽዕኖውን ሊቋቋሙት ይችላሉ ብለዋል።
ይሁን እንጂ ተመራማሪዎቹ እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወፎቹ ዝርያዎች በርካታ ጥቃቅን ተጽኖዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
በአንጻሩ ግን ሌሎች ዝርያዎች ከአካባቢያዊ እና ክልላዊ ለውጦች ማምለጥ እንደማይችሉ አስጠንቅቀዋል።
ዋነኛ ጥያቄው እነዚህ ወፎች ሌሎች ወፎች የሌላቸው ምን አሏቸው? የሚለው ሆኗል። ተመራማሪዎቹ የባህር ወፎች መጥፎ ሁኔታዎች ያላቸውን ቦታዎች በመቀየር ይችላሉ ብለዋል።
የዚህ አይነቱ እንቅስቃሴ በዚህ መጠን በሌሎች ዝርያዎች ምናልባትም ብዙም ያልተለመደ ነውዐሲሉ ምክንያት አንስተዋል።
ወፎቹ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ለመላመድ መንቀሳቀስ ቁልፍ ሊሆን እንደሚችል ለሰው ልጆች ማስተማር እንደሚችሉም አንስተዋል።
ተመራማሪዎቹ የባህር ከፍታ ሲጨምር ፣ አውሎ ነፋሶች እየጠነከሩ እና የሙቀት መጠኑ እየጨመረ ሲመጣ ሰዎች በምድር ዙሪያ መንቀሳቀስ ሲጀምሩ መቋቋም ያዳብራሉ ብለዋል።