የአየር ንብረት ለውጥ በአሳ ብዝሃ ህይወት ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አለው?
የሆንግ ኮንግ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ሙቀት ወቅት የአሳ ህይወት ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ጥናት አድርጓል
የአለም ሙቀት በዚሁ ከቀጠለ የአሳዎች ሞት በቀጣይ 70 አመታት በ34 እጥፍ ይጨምራል ተብሏል
አለማችን እያስተናገደችው ያለው የአየር ንብረት ለውጥ በየትኛውም ፍጥረት ላይ ጉልህ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው።
የውቅያኖሶች አሲዳማነት እና የውሃ ሙቀት መጨመር የአሳ ሃብት እንዲመናመን እያደረገ ይገኛል።
በከፍተኛ ሙቀት ወቅት ውቅያኖሶች አምቀው የሚይዙት ሙቀት እና ካርበን ዳይ ኦክሳይድ ስለሚጨምር በሚሊየኖች የሚቆጠሩ አሳዎች በዳርቻዎች ላይ ሞተው ታይተዋል።
የአለም ሙቀት በዚሁ ከቀጠለ በጅምላ ሞተው የሚገኙ አሳዎች ቁጥር ከ70 አመት በኋላ በ34 በመቶ እንደሚጨምር የአርካንሰስ ዩኒቨርሲቲ በ2022 ይፋ ያደረገው ጥናት ማመላከቱ የሚታወስ ነው።
በጃፓን የሚገኘው የሆንግ ኮንግ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ጥናትም የአሳ ብዝሃ ህይወት በአየር ንብረት ለውጥ ምን አይነት ተጽዕኖ እየደረሰበት እንደሚገኝ አመላክቷል።
በጃፓን ቦሶ ልሳነ ምድር በ11 ውሃማ ክፍሎች ለ2 አመት የተሰበሰበ መረጃን መሰረት አድርጎ የተከናወነው ጥናት በከፍተኛ ሙቀት ወቅት የአሳዎች የእርስ በርስ ግንኙነት እንደሚጨምር አረጋግጧል።
በከባድ ሙቀት ግንኙነታቸው የሚጨምር የአሳ ዝርያዎች ተመሳሳይ መሆናቸውን የሚጠቅሰው ጥናቱ፥ የተለያየ ዝርያ ያላቸው አሳዎች ይበልጥ ግን ይበልጥ ይራራቃሉ ብሏል።
ይህን የተለያየ ዝርያ ያላቸው የአሳ አይነቶች ግንኙነት የመጠናከርና የመላላት ጉዳይ በአንክሮ መመልከት በውቅያኖሶች እና ባህር ውስጥ የሚገኘውን የአሳ ብዝሃ ህይወት ለመጠበቅ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል።
ጥናቱ በተለይ የአሳ ሃብትን በብዛት የሚጠቀሙ አካላት የትኛውን አይነት አሳ ማራባት አዋጭ መሆኑን እንዲገነዘቡም እድል የፈጠረ ነው ተብሏል።
በከፍተኛ ሙቀት ወቅት የእርስ በርስ ግንኙነታቸው የሚጨምር ተመሳሳይ የአሳ አይነቶች የትኞቹ እንደሆኑ በዝርዝር ያስቀመጠው ጥናቱ በገበያ ላይ የማይገኙ የአሳ አይነቶችን እንዴት ማብዛት እንደሚቻልም ፍንጭ ሰጥቷል።