ከባድ ዝናብ እና የአየር ንብረት ለውጥ
ከባድ ዝናብ ሊያስከትለው የሚችለው አንዱ ችግር ድንገተኛ ጎርፍ ነው
የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀትን በመሰሉ የሰው አስተዋጽኦ የሚባባስ የአየርንብረት ለውጥ የአለም የሙቀት መጠን እንዲጨምር ማድረጉ እሙን ነው
በቅርብ አመታ ውስጥ አለም ከባድ ዝናብ በተደጋጋሚ እየተከሰተባት ነው። ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደጋገም ከባድ ዝናብ በሰው፣ በመሰረተልማት እና በአካባቢ ላይ ጉልህ የሆነ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እንዲህ አይነት ዝናብ የሚጠበቅ ቢሆንም መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግን የአየርንብረት ለውጥ ድግግሞሹን እንዳባባሰው እና ጥንካሬው እንዲጨምር አድርጓል።
የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀትን በመሰሉ የሰው አስተዋጽኦ የሚባባስ የአየርንብረት ለውጥ የአለም የሙቀት መጠን እንዲጨምር ማድረጉ እሙን ነው።የመሬት ሙቀት መጠን ሲጨምር እርጥበት ስለሚይዝ የዝናብ መጠን ይጨምራል። ይህ ክስተት እና የአየርንብረት መዛባት ከፍተኛ ዝናብ እንዲከሰት ምክንያት ይሆናሉ።
ከባድ ዝናብ ሊያስከትለው የሚችለው አንዱ ችግር ድንገተኛ ጎርፍ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ በሚኖርበት ጊዜ ወንዞች ተፋሰሶች እና ምንጮች ከአቅማቸው በላይ ስለሚሆን ድንገተኛ እና አደገኛ ጎርፍ እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል። ጎረፉም በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ያስትላል።
ከዚህ በተጨማሪም ከባድ ዝናብ በተለይም በተራራማ እና ዳገታማ ቦታዎች የመሬት መንሸራተት እና የናዳ አደጋ እንዲከሰት ያደርጋል።
የአየርንብረት ለውጥ የከባድ ዝናብ ተጽዕኖዎች በእነዚህ አይወሰንም።
በስነ-ህይወት እና በስነ-ምህዳር ላይ የረጅም ጊዜ ተጽእኖ ያሳድራል። ከፍተኛ ዝናብ የአፈር ለምነት እንዲሸረሸር፣ የማዐሰድን መጠኑ እንዲቀንስ እና የእጽዋት እና እንሰሳት መሰናሰንን ይቀይራል።