የአየር ንብረት ለውጥ በ2070 በሽዎች የሚቆጠሩ ቫይረሶች እንዲሰራጭ ያደርጋል ተባለ
ይህም ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ተላላፊ በሽታዎችን የመጋለጥ እድልን ይጨምራል ተብሏል

አሮጌ እና አዲስ በሽታዎች በብዛት እየተስፋፉ ከመሆናቸውም በላይ ቀደም ሲል ባልተገኙባቸው ቦታዎችም እየታዩ ነው።
የአየር ንብረት ለውጥ እ.አ.አ. በ2070 በሽዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ቫይረሶች በእንስሳት ዝርያዎች ውስጥ እንዲስፋፉ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ንደሚችል ተገለጸ።
ይህም ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ተላላፊ በሽታዎችን የመጋለጥ እድልን ይጨምራል ተብሏል።
በዓለም ዙሪያ ሰዎች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በፊት ከነበሩት የበለጠ ረጅም እና ጤናማ ህይወት እየኖሩ ቢሆንም፤ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ይህንን እድገት ለመቀልበስ ያሰጋል።
የአየር ንብረት ለውጥ በየዓመቱ መኖሪያ ቤት፣ ህክምናና ምግብ በሚሹ 20 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎችን ያፈናቅላል።
በሽታ አምጪ እንስሳት እነዚህን ለውጦቹን ለማስተናገድ እየገቡ ነው።
አንበጣ፣ ትንኞች፣ ባክቴሪያ፣ አልጌ እና ፈንገሶችም በሽታ ወደ ሰው ያስተላልፋሉ። ታሪካዊ ክልላቸውን እየቀየሩ ወይም እያስፋፉ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሻሻለ ካለው የአየር ንብረት ሁኔታ ጋር ይጣጣማሉ።
የደን መጨፍጨፍ፣ ማዕድን፣ ግብርና እና የከተሞች መስፋፋት በዓለም ላይ የቀሩትን የዱር አካባቢዎች እያሟጠጡ ሲሆን፤ ይህም በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየደረሰ ላለው የብዝሃ ህይወት መጥፋት አስተዋጽኦ አድርጓል።
እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ለበሽታ ከፍተኛ ሁኔታዎችን ይፈጥራሉ።
አሮጌ እና አዲስ በሽታዎች በብዛት እየተስፋፉ ከመሆናቸውም በላይ ቀደም ሲል ባልተገኙባቸው ቦታዎችም እየታዩ ነው።
ተመራማሪዎች ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአየር ንብረት ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በሰው ጤና ላይ የሚያደርሱትን ከፍተኛ ስጋት - እና ሊመጡት የሚችሉትን አደጋዎች የሚያመላክቱ መረጃዎችን አዘጋጅተዋል።
ኮንሰርቬሽን ኢንተርናሽናል የተሰኘው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት፤ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለው ውጤት ወደፊት የሚመጣ ብቻ ሳይሆን፤ አሁን ያለና ሰዎች እየተሰቃዩና እየሞቱ ነው ብሏል።