የአየር ንብረ የፍላጎት ጉባኤ በስምንት ሀገራት ለህይወት አድን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ሊዘረጋ ነው
የቅድመ ማስጠንቀቂያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስርዓትን ለመዘርጋት 157 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ተገልጿል
ኢትዮጵያን ጨምሮ በስምንት ሀገራት የሚተገበረው ስርዓት አደጋ ከመከሰቱ ከ24 ሰዓት በፊት ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ነው
የመንግስታቱ ድርጅት ኤጄንሲዎችና ሌሎች አጋሮች አዲስ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ይፋ አድርገዋል።
ዘመቻው ኒዮርክ በተደረገውና በ2027 የቅድመ ማስጠንቀቂያ ይፋ ቀሆነው የአየር ንብረ የፍላጎት ጉባኤ ነው።
በጉባኤው ለህይወት አድን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ለማቋቋም ተመድ የልማት ፕሮግራም ግዙፍ የትብብር የልማት ዘመቻ አስታውቋል።
- ለዓለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ለመስጠት 2 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ
- የአየር ንብረት ቀውስ "የገሃነምን በር ከፍቷል"- የተመድ ዋና ጸኃፊ
ስርዓቱ በአየር ንብረት ለውጥ ክፉኛ በሚጠቁ የዓለም ሀገራት እንደሚጀመር ተነግሯል።
እርምጃው በ2027 መጨረሻ በቅድመ ማስጠንቀቂያ እያንዳንዱ የዓለም ዜጋ ከከባድ አደጋ፣ ከባቢና አየር ንብረት ሁነቶች እንዲጠበቅ የማድረግ ፍላጎት አካል ነው ተብሏል።
የቅድመ ማስጠንቀቂያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስርዓትን ለመዘርጋት 157 ሚሊዮን ዶላር እንደሚመደብ ተገልጿል።
የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራምና ሌሎች ለጋሽ አጋሮች የእርምጃውን ስፋት ለማሰደግ ትብብር ተጠይቋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በሰባት ሀገራት የሚተገበረው ስርዓት አደጋ ከመከሰቱ ከ24 ሰዓት በፊት ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ነው።
ስርዓቱ እንደ ጎርፍና እሳት የመሰሉ አደጋዎች የሚያደርሱትን ጉዳት በ30 በመቶ እንደሚቀንስ ተነግሯል።