በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ዝግጅት ወደ 500 የሚጠጉ ሰራተኞች በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን አጥተዋል ተባለ
ከዚህ ቀደም በስታዲየሞች ግንባታ ከስራ ጋር በተገናኘ የሦስት ሰዎች ብቻ ህይወታቸው ማለፉ ተነግሮ ነበር
የዘንድሮ የዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ ኳታር በሰራተኞች ሞት የግልጸኝነት ጉድለት አሳይታለች በሚል ክስ ቀርቦባታል
የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫን ያሰተናገደችው ኳታር ከዋንጫው ጋር በተያያዙ ፕሮጀክቶች የሞቱት ስደተኛ ሰራተኞች ቁጥር "ከ400 እስከ 500" መካከል ነው ብላለች።
የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ የጠቅላይ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ ሀሰን አል ተዋንዲ ሀገሪቱ ስትተችበት የከረመችውን የሰራተኞች ሞት አምነዋል።
ነገር ግን ዋና ጸሀፊው የሟቾች ትክክለኛ ቁጥርን አሁንም "በመነጋገር ላይ ነን" ብለዋል። "ግምቱ በ400 እና 500 መካከል ነው ሲሉ ዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት በተሰሩ መሰረተ ልማቶች ህይወታቸው ያለፉ ሰራተኞችን ጉዳይ ገልጸዋል።
"ትክክለኛው ቁጥር የለኝም። ይህ እየተነጋገርን ያለነዉ ነገር ነው" ብለዋል።
"አንድ ሞት በጣም ብዙ ነው" በማለት ኳታር በተለይም በምዕራቡ ዓለም የደረሰባትን ትችት አስተያየት ተሰጥተዋል።
ነገር ግን ያሉት ዋና ጸሀፊው በየዓመቱ በዓለም ዋንጫ ጣቢያዎች ላይ የጤና እና የደህንነት ደረጃዎች እየተሻሻሉ ነው ብለዋል።
የውድድሩ ግንባታ በፈረንጆቹ 2014 ከተጀመረ ወዲህ በአለም ዋንጫ ስታዲየሞች ስደተኛ ሰራተኞች ከስራ ጋር የተገናኙ ሦስት ሰዎች ብቻ ህይወታቸው ማለፉን እንዲሁም። 37 ሰዎች ደግሞ ከስራ ጋር ባልተያያዘ መሞታቸውን ጠቅላይ ኮሚቴው አስታውቆ ነበር።