ስፖርት
ፊፋ በኳታር ዓለም ዋንጫ ሰባት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገለጸ
የኳታሩ ገቢ ከ2018ቱ የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ጋር ሲነጻጸር አንድ ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል
ተጨማሪ ገቢው ከዓለም ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ኳታር ጋር በተደረገ የንግድ ስምምነት ነው
የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ መሪ ፊፋ ለአባል ፌዴሬሽኖች ከኳታር የ2022 ዓለም ዋንጫ ጋር በተገናኘ በአራት ዓመታት የንግድ ስምምነቶች ክብረ ወሰን ነው የተባለ ሰባት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ተናግሯል።
ፊፋ ገቢውን ከ200 በላይ አባላት ለተውጣጡ ባለስልጣናት ነው ይፋ ያደረገው።
የኳታሩ ገቢ ከ2018ቱ የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ጋር ሲነጻጸር ገቢ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል።
ተጨማሪ ገቢው ከዓለም ዋንጫ አዘጋጇ ሀገር ጋር በተደረገ የንግድ ስምምነት የተገኘ መሆኑን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
"ኳታር ኢነርጂ" ከፍተኛ ደረጃ የስፖንሰር ዝርዝርን ተቀላቅሏል የተባለ ሲሆን፤ አዲስ የሶስተኛ ደረጃ ስፖንሰሮች የኳታር ባንክ እና የቴሌኮም ኩባንያን ያካትታሉ ተብሏል።
ለዚህ የዓለም ዋንጫ አብዛኛው የስርጭት ስምምነቶች የተፈረሙት በፈረንጆቹ በ 2011 ሴፕ ብላተር ፕሬዝዳንት በነበሩበት ጊዜ ነው። ስምምነቶቹ የሩስያ እና የኳታር ውድድሮችን ያካተቱ እንደነበሩ ተነግሯል።