ቁጥሮች የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ስለሆነችው ትንሿ ሀገር ኳታር ምን ይላሉ?
የአለም ዋንጫን የምታዘጋጀው ኳታር ስፋት የለንደን ከተማን አታክልም
ከ3 ሚሊየን ገደማ የሚኖርባ ሲሆን፤ የኳታር ዜጎች ከ300 ሺህ አይበልጡም
ኳታር ከ200 ቢሊየን ዶላር ወጪ ያደረገችበት ግዙፉ የዓለም የእግር ኳስ መድረክ የ2022 የዓለም ዋንጫ አዘጋጅታለች።
ውድ የዓለም ዋንጫን ስላዘጋጀቸው ትንሿ ሀገር ኳታር ቁጥሮች ምን ይላሉ?
ኳታር በፈረንጆቹ 1971 ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነፃ ወጥታለች። የአልታኒ ቤተሰብ ከ1825 ጀምሮ ኳታርን እየመራ ነው።
- በዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፈው ኳታር ብሄራዊ ቡድን ዝግጅት ምን ይመስላል?
- ትኬት የሌላቸው ደጋፊዎች የ2022 የዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ ኳታር መግባት እንደሚችሉ ተገለፀ
ኳታር 3 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ይኖርባታል። ከአጠቃላይ ነዋሪው ግን የሀገሪቱ ዜጋ ከ300 ሺህ አይበልጥም። ከ100 በላይ ሀገራት ዜጎች ይኖሩባታል።
ከ80 በላይ ሀገራት ያለቪዛ መግባት ይችላሉ፤ ይህም ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት አንደኛ ከአለም 8ኛ ደረጃን እንድትይዝ አድርጓታል።
97 በመቶው የተማረ ህዝብ ያለባት ሲሆን፥ የሴቶች እጥረት ግን በስፋት ይስተዋልባታል፤ ከጠቅላላው ህዝብ 24 ነጥብ 7 በመቶው ብቻ ነው ሴት።
ኳታር ወንጀል ከማይፈፀምባቸው ሀገራትም ከ153 ሀገራት 31ኛ ደረጃን በመያዝ ሰላማዊነቷ ተመስክሮላታል።
በየብስ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ብቻ የምትዋሰነው ሀገር ስፋቷ ለንደንን አያክልም፤ የአሜሪካዋን ኒውዮርክ ከተማም 10 በመቶ ብቻ ነው የምትሸፍነው፤ 160 ኪሎ ሜትር ከሰሜን እስከ ደቡብ 80 ኪሎሜትር ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ትረዝማለች።
አራት ማዕዘኗ ሀገር ደሴት ሳይሆኑ ጠባብ ከሆኑ ሀገራት 11ኛ ደረጃ መያዟንም መረጃዎች ያመላክታሉ። በአሳ ሀብቷ የምትታወቀው ዶሃ የተፈጥሮ ጋዝና የነዳጅ ክምችቷ የእድገት ግስጋሴዋን አፋጥኖታል።
ከሩስያና ኢራን በመቀጠል 3ኛዋ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ያለባት ኳታር ለተከታታይ አመታት ፈጣን እድገት አስመዝግባለች።
የሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ወይም (ጂ ዲ ፒ) 216 ቢሊየን ደርሷል። ከ62 ሺ ዶላር በላይ የደረሰው የነፍስ ወከፍ ገቢም ከአለማችን ባለጠጋ ሀገራት ከፊት አሰልፏታል።
229 ቢሊየን ዶላር ወጪ አድርጋ በ8 ስታዲየሞች ያዘጋጀችውን የአለም ዋንጫ ለማቅረብም ስአታት ቀርተዋል።