ልዩልዩ
በኳታር የዓለምን ቀልብ የሳበው "የሜትሮ ጠቋሚ"
ማማ ላይ ሆኖ የባቡር መሳፈሪያ አቅጣጫን የሚያመላክትበት ቪዲዮ ቲክቶክንና ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን አጥለቅልቋል
የማህበራዊ ሚዲያው በተለይም ቲክቶክ በዚሁ የኳታር የአለም ዋንጫ ክስተት ተሞልቷል
ኳታር ለአለም ዋንጫው የቀጠረችው ሰራተኛ የማህበራዊ ሚዲያው የሰሞኑ ትኩረት ሆኗል።
ማማ ላይ ሆኖ የእግር ኳስ ደጋፊዎችን የባቡር መሳፈሪያ አቅጣጫን የሚያመላክትበት ቪዲዮ ነው ቲክቶክን ያጥለቀለቀው።
ትልቅ የስፓንጅ አቅጣጫ መጠቆሚያ ይዞ "ሜትሮ" "ሜትሮ" "ሜትሮ" እያለ ደጋግሞ በድምፅ ማጉያ የሚናገረውን ወጣት ቪዲዮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አስመስለው ሰርተውታል።
እግር ኳስ ተጫዋቾች እና ብሄራዊ ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ኳታር የዘለቁ ደጋፊዎችም ሰብሰብ ብለው "ሜትሮ በዚህ አቅጣጫ ነው" እያሉ ቪዲዮውችን ለቀው ሚሊየኖች ተመልክተዋቸዋል።
ፈገግ የሚያሰኘው ቪዲዬ የበርካቶችን የዛለ መንፈስ ስለማነቃቃቱ ሜትሮ ዘግቧል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎችም አሁን ከሜሲ ይልቅ ይህ ልጅ ታዋቂ ነው" እስከማለት ደርሰዋል።
በርካቶች አሁንም ድረስ ስሙ ያልተጠቀሰውን ወጣት የኳታር የአለም ዋንጫ ማድመቂያ አድርገውታል።