የእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን በጎርፍ ተወስደዉ የነበሩ ወጣቶችን አተፈረ
ወጣቶቹ የ 18 እና የ 19 ኣመት ወጣቶች ናቸው
ከትናንት በስቲያ ሁለት ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል
በአዲስ አበባ ከተማ በጎርፍ የተወሰዱ ወጣቶችን ማዳኑን የከተማዋ እሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 10 እሪ በከንቱ አካባቢ በሚገኝ ወንዝ ውስጥ የገቡ ወጣቶችን ማዳን መቻሉን ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።
ወጣቶቹ 18 እና 19 ዓመታቸው ሲሆን፤ ያገለገሉ ፕላስቲኮችንና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለመልቀም ወንዝ ዉስጥ እንደገቡ አቶ ንጋቱ ገልጸዋል።
ወጣቶቹ በድንገት ደራሽ ጎርፍ መጥቶባቸዉ ህይወታቸዉ አደጋ ላይ ቢወድቅም ከወንዙ ዉስጥ ግን ማውጣት ተችሏል።
ወጣቶቹ ለ25 ደቂቃ ያህል ከጎርፉ ጋር ሲታገለ ነበር ተብሏል።ቆይተዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ዋናተኞች በዋና ገብተዉ የወጣቶቹን ህይወት ማትረፋቸውን አቶ ንጋቱ ማሞ ለአል ዐይን አማርኛ አስታውቀዋል።
በከተማዋ በተለያዩ ወንዞች ዉስጥ በመግባት ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በመሰብሰብና በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች በዚህ በክረምት ጊዜ በወንዝ አካባቢ ያሏቸውን እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙሏሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በተመሳሳይ ታዳጊዎችና ህጻናት ጎርፍ ያመጣቸዉን ቁሳቁሶች ለማዉጣት ወንዝ ዉስጥ ለመግባት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም እንዲያቆሙና ወላጆችም ልጆቻቸዉን እንዲጠብቁ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡
ከትላንት ወዲያ ዕሁድ ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ጎርፍ ያመጣዉን ኳስ ለማዉጣት በወንዝ ዉስጥ የገቡ የ9 እና የ 14 አመት ታዳጊዎች ህይወታቸዉ እንዳለፈ ይታወሳል፡፡