ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራተኛ የቀነሱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የትኞቹ ናቸው?
ኩባንያዎቹ ምን ያልህ እንደቀነሱ የስራተኛ ቅነሳን በሚከታተለው ሌይኦፍስ.ኤፍዋይአይ መረጃ መሰረት በደረጃ ተቀምጠዋል
ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራተኛ የቀነሰው ዴል ነው
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራተኛ የቀነሱ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የትኞቹ ናቸው?
በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለው የሰው ኃይል ቅነሳ የተጀመረው ዲስኮርድ፣ ዩኒቲ እና ቲስዊች በመሳሰሉት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ነው።
ከአመታት በኋላ ግን ሌሎች ኩባንያዎችም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞቻቸውን መቀነሳቸውን የቪዢዋል ካፒታሊስት መረጃ ያመለክታል።
ከስር የተዘረዘሩት ኩባንያዎች ከ2024 ከጀመረ አንስቶ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ምን ያልህ እንደቀነሱ የስራተኛ ቅነሳን በሚከታተለው ሌይኦፍስ.ኤፍዋይአይ መረጃ መሰረት በደረጃ ተቀምጠዋል።
ዴል
ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራተኛ የቀነሰው ዴል ነው። ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ ኩባንያው 26ሺ ሰራተኞቹን ወይም የአጠቃላይ ሰራተኞቹን 20 በመቶ ቀንሷል
ኢንቴል
ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለው 15 ሺ ሰራተኞቹን የቀነሰው ቺፕ የሚያበለጽገው እና የሚያመርተው ኢንቲል ኩባንያ ነው። ኩባንያው የቀነሰው የሰው ኃይል የአጠቃላይ የሰው ኃይሉን 15 በመቶ እንሚያህል ነው ተብሏል።
ቴስላ
ስስተኛ ደረጃ የያዘው 14500 ሴራተኞቹን ወይም የአጠቃላይ የሰው ኃይሉን 10 በመቶ የቀነሰው የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ ነው።
ሲስኮ
ሰራተኛ በመቀነስ አራተኛ ደረጃ ላይ ያለው ሲስኮ ነው። የኔትወርክ መሳሪያዎቸን እና ሶፍትዌሮችን የሚያመርተው 10,150 ሰራተኞቹን ወይም የአጠቃላይ የሰው ኃይሉን 12 በመቶ ቀንሷል።
ሳፕ
አምስተኛ ደረጃ ላይ ያለው የጀርመኑ የሶፍትዌር ኩባንያ ሴፕ ነው። ሴፕ 8ሺ ሰራተኞቹን ወይም ከአጠቃላይ የሰው ኃይሉ 12 በመቶ የሚሆነውን ቀንሷል።