ተመድ ገንዘብ የዓለምን ረሃብ እንዴት እንደሚፈታ ካስረዳኝ የቴስላን አክሲዮን በመሸጥ ገንዘቡን አስጣለሁ- ኤሎን መስክ
ከቴስላ የ1 ቀን ገቢ 1/6ኛው ረሃብ በራቸውን የሚያንኳኳ 42 ሚሊየን የዓለማችን ህዝብን መታደግ እንደሚቻል ተመድ ገልጿል
ኤሎን መስክ በ236 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ሀብት የዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር መባሉ ይታወሳል
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ሞተርስ ባለቤት የሆነው ኤሎን መስክ ቁጥር አንዱ የዓለማችን ቱጃር መሆኑ ይታወቃል።
ኤሎን መስክ ጄፍ ቤዞስን በመብለጥ የዓለማችን ቁንጮ ቱጃር መሆን የቻለ ሲሆን፤ የቱጃሮቹን ሃብት የሚያሰላው ብሉምበርግ በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ዘርፍ ላይ የተሰማራው መስክ የተጣራ 236 ቢሊየን ዶላር አለው ማለቱም ይታወሳል።
ኤሎን መስክ የዓለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ሊሆን የቻለው በአንድ ቀን ባገኘው 36 ቢሊየን ዶላር እንደሆነ ነው በሉመበርግ ያሰፈረው።
ይህንን ተከትሎም የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ በትዊተር ገጻቸው ኤለን መስክን እንኳን ደስ አለህ ካሉት በኋላ፤ “በአንድ ቀን በካገኸው ገቢ 1/6ኛው ረሃብ በራቸውን እያንኳኳ የሚገኝ 42 ሚሊየን የዓለማችን ህዝብን መታደግ ይችላል” ብለው ነበር።
ይህንን ተከትሎም ባለሀብቱ ኤሎን መስክ በትዊተር ገጻቸው በሰጡት ምላሽ፤ “የዓለም ምግብ ፕሮግራም በዚህ የትዊተር ላይ 6 ቢሊየን ዶላር የዓለምን ረሃብ እንዴት እንደሚፈታ በትክክል መግለጽ ከቻለ የቴስላን ድርሻ አሁኑኑ እሸጣለሁ፤ ገንዘቡንም እለግሳለሁ” ብለዋል።
“ሆኖም ግን ገንዘቡ ግልፅ እና ተጠያቂነት ባለው መልኩ መውጣት አለበት፤ በዚህ መልኩ ህዝቡም ገንዘቡ ምን ላይ እንደዋለ ማወቅ ይችላል” ብሏል።
የዓለም ምግብ ፐሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ ለኤሎን መስክ ትዊት በሰጡት ምለሽ፤ “6 ቢሊየን ዶላር የዓለምን የረሃብ ችግር አይፈታም ነገር ግን የጂኦ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን፣ ስደተኝነትን እና የረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙ 42 ሰዎችን ከአደጋ ሊከላከል ይችላል” ሲሉ አስታውቀዋል።
“ባንተ ድሃፍ ጋር ለዓለም ተስፋን ማምጣትን ጨምሮ፣ መረጋጋትን ለመገንባት እና ለወደፊት ለውጥ ማምጣት ይቻላል፤ ስለዚህ እንነጋገርበት” ብለዋል።
“ይህ ጉዳይ ይህን ያክል ከባድ እና የተወሳሰበ አይደለም፤ ከተስማማክ በቀጣይ በረራ ወዳአንተ እመጣለሁ፤ የሰማኸው ነገር ካተስማማክ ልታባርረኝ ትችላለክ” ሲሉም ጽፈዋል።