በ2030 የበካይ ጋዝ ልቀት በ43 በመቶ መቀነስ አለበት- የኮፕ28 ፕሬዝደንት
ከ198 ሀገራት በላይ የተወከሉበት በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 ስብሰባ ዛሬ አምስቸኛ ቀኑን ይዟል
ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት ሚቴን የተባለውን ዋነኛ በካይ ጋዝ ለመቀነስ የሚያስችል ፈንድ ከአሜሪካ እና ከቻይና ቃል ተገብቶላቸዋል
የኮፕ ፕሬዝደንት በ2030 የበካይ ጋዝ ልቀት በ43 በመቶ መቀነስ አለበት ብለዋል።
የአረብ ኢሜሬትስ የኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ እና የኮፕ28 ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን አህመድ ቢን አልጃብር አለምአቀፍ የበካይ ጋዝ ልቀትን በ2030 በ43 በመቶ ወይም 22 ጊጋቶን መቀነስ እንዳለበት ተናግረዋል።
ዶክተር አል ጃብር በሰጡት መግለጫ በመጀመሪያ ቀን አጀንዳ ያጸደቀ የአየር ንብረት ስብሰባ የለም፣ የዚህ አመት ስብሰባ ታሪካዊ መሆኑን የሚክድም የለም ሲሉ ተናግረዋል።
ዶክተር ጃብር "ለሎስ ኤንድ ዳሜጅ ወይም ለካሳ የሚሆን 258 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ መድበናል እና ለዚሁ ጉዳይ ልዩ ስብሰባ እንዲደረግ ጠይቀናል" ብለዋል።
የኮፕ28 ፕሬዝደንት የ'ሄልዝ እና ዳይት' ዲክላሬሽን ይፋ በመሆኑ የተማቸውን ኩራት ገልጸዋል።
ፕሬዝደንቱ እንደገለጹት ሚቴን የተባለውን ዋነኛ በካይ ጋዝ ለመቀነስ የሚያስችል ፈንድ ከአሜሪካ እና ከቻይና ቃል ተገብቶላቸዋል።
ከ198 ሀገራት በላይ የተወከሉበት በአረብ ኢምሬትስ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 ስብሰባ ዛሬ አምስቸኛ ቀኑን ይዟል።