የአየር ንብረት ለውጥ ወደ ከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ሀገራት ምን ያድርጉ?
ማህበረሰቡ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እንዲሰራ ማስተማር እና ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው
መወሰድ ከሚገባቸው እርምጃዎች ውስጥ የሚከተሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው
የአር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለው ችግር የከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ሀገራት በርካታ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እርምጃዎች አሉ።
መወሰድ ከሚገባቸው እርምጃዎች ውስጥ የሚከተሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው።
1) ቀደም ብሎ ብክለት መቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ
ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም የካርቦን ልቀትን መቀነስ እና ኢንዱስትሪዎች ዘላቂ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ
2) ብክለትን የመቋቋም ዘዴዎችን መጠቀም
ውሃን በአግባቡ በመጠቀም እና ቻይ የሆነ መሰረተልማት በመገንባት ለማይቀረው የአየር ንብረት ተጽዕኖ መዘጋጀት
ብክለትን በመቋቋም ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ተግባራዊ ማድረግ
3) አለምአቀፍ ትብብር
ቴክኖሎጂን ለመጋራት፣ ተጋላጭ የሆኑ ሀገራትን ለመርዳት እና የአየር ብክለት ቅነሳ ግቦችን ለማስቀመጥ አለምአቀፍ ትብብር ማድረግ ወሳኝነት አለው
4) በፈጠራ ስራዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ
የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ በሚያስችሉ የፈጠራ ስራዎች፣ ጥናት እና ቴክኖሎጂዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ያስለፈልጋል። አረንጓዴ ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ዘላቂ መፍትሄን ለማምጣት ይረዳል።
5) የህዝብ ተሳትሮ እና ትምህርት
ማህበረሰቡ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እንዲሰራ ማስተማር እና ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው
በአጠቃላይ ብክለትን ለመቀነስ የሚረዱ ቁልፍ የሚባሉ ተግባራትን ጊዜ ሳይወስዱ መተግበር አስከፊ የሆኑ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን ለመቋቋም ያስችላል።