ፖለቲካ
አረብ ኢምሬትስ ለአየር ንብረት መፍትሄዎች ያቋቋመችው ፈንድ በውስጡ ምን ይዟል?
አረብ ኢምሬትስ ለአየር ንብረት መፍትሄዎች የ30 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሟን አስታውቃለች
የ28ኛው የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) በዱባይ እየተካሄደ ነው
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ ሀገራቸው ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎች የ30 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሟን ትናንተ አስታውቀዋል።
ለአየር ንብረት መፍትሄዎች ፈንድ የተቋቋመው የአየር ንብረት ፋይናንስ ክፍተቱን ለመሙላትና እና ገንዘቡ በተገቢው መልኩ ተደራሽነቱን ለማመቻቸት ነው ብለዋል።
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አክለውም የገንዘብ እጥረት በዓለም አቀር የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎች ላይ ትልቁ እንቅፋት መሆኑንም አብራርተዋል።
የአየር ንብረት መፍትሄዎች ያቋቋመችው ፈንድ በውስጡ ምን ይዟል?