የዓለም ቢዝነስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ 5 ቢሊዮን ዶላር አዋጡ
በዓለም ላይ የሚደርሱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በየዓመቱ 100 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል
28ኛው የተመድ አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በዱባይ እየተካሄደ ይገኛል
የዓለም ቢዝነስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ድጋፍ 5 ቢሊዮን ዶላር አዋጡ
በአረብ ኢምሬት አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አራተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየዓመቱ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የዓለም ሀገራት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያዎችን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት ጋር በመምከር ላይ ይገኛል፡፡
የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራች እና ባለቤት የሆኑት ቢል ጌትን ጨምሮ በርካታ የቢዝነስ ሰዎች በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ የቢዝነስ ተቋማት መሪዎች ባደረጉት ውይይት የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመከላከል አምስት ቢሊዮን ዶላር እንደሚያዋጡ አስታውቀዋል፡፡
የበለጸጉ ሀገራት በኢንዱስትሪዎቻቸው በሚለቁት በካይ ጋዝ ምክንያት ታዳጊ ሀገራት ላይ በሚደርስ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ያልተገባ ጉዳት እያስተናገዱ እንደሆነም ተገልጿል።
የአፍሪካ ተደራዳሪ ቡድን የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ፈንድ መቋቋሙን አወደሰ
በርካታ ሀገራት ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ማካካሻ ፈንድ ገንዘብ በማዋጣት ላይ ሲሆኑ ይህ ፈንድ በዓመት 100 ቢሊዮን ዶላር ከሀገራት እና ተቋማት ለመሰብሰብ እና የተጎዱ ሀገራትን እንደሚክስ ይጠበቃል፡፡
አረብ ኢምሬት ለዚህ ፈንድ 100 ሚሊዮን ዶላር ስታዋጣ፣ አሜሪካ 17.5 ሚሊዮን ዶላር፣ ብሪታንያ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ፣ ጃፓን 10 ሚሊዮን ዶላር፣ የአውሮፓ ህብረት ደግሞ 145 ሚሊዮን ዩሮ በድምሩ ለፈንዱ በሁለት ቀናት ውስጥ 400 ሚሊዮን ዶላር መዋጣቱ ተገልጿል።