28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ(ኮፕ28) - ዱባይ
ለ12 ተከታታይ ቀናት መላው አለምን እየፈተነ ስለሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥ የሀገራት መሪዎችና ባለሙያዎች የሚመክሩበት ኮፕ28 ዛሬ ይጀመራል
በጉባኤው ታሪካዊ ስምምነቶች እንደሚፈረሙ ይጠበቃል
28ኛው የመንግስታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በዛሬው እለት በአረብ ኤምሬትሷ ዱባይ ይጀመራል።
የኮፕ28 ጉባኤ በይፋ ሲከፈት የኮፕ27 ፕሬዝዳንት የነበሩትና የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ የመክፈቻ ንግግር ያደርጋሉ።
ሚኒስትሩ ዶክተር ሱልጣን አል ጀበር የ28ኛው የመንግስታቱ ድርጅት የአየርንብረት ለውጥ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸውን የጉባኤው ተሳታፊዎች በጭብጨባ እንዲገልጹም ያደርጋሉ።
በመቀጠልም የኮፕ28 ፕሬዝዳንት የጉባኤው አጀንዳዎች የሚያጸድቁ ሲሆን በ2026 እና 2027 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤዎችን የሚያዘጋጁ ሀገራት ምርጫ ይካሄዳል።
ከ97 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እና ከ400 ሺህ በላይ ጎብኝዎች የሚታደሙበት 28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለ12 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።
በጉባኤው የ167 ሀገራት መሪዎች እንደሚታደሙና ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። የጉባኤውን ዋና ዋና አጅንዳዎች ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ