የተመድ ባለሞያዎች ፋኦ በኮፕ 28 ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ገለጹ
ግብርና ለምግብ ዋስትና እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመጋፈጥ መፍትሄዎችን ይሰጣል
ፋኦ በርካታ ውጥኖች እና መርሀ-ግብሮች አረብ ኤምሬቶች ከምታዘጋጀው ኮፕ 28 በፊት ይቀርባል
ግብርና ለምግብ ዋስትና እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመጋፈጥ መፍትሄዎችን ይሰጣል።
የአየር ንብረት ለውጥ የኑሮ ሁኔታዎችን የሚጎዳ እና የምግብ ዋስትናን አደጋ ላይ የሚጥል ሲሆን፤ የግብርና ምርትን ለመጨመር ያልተለመዱ መፍትሄዎችን መፈለግንም ይጠይቃል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ልዩ አማካሪ ጂንጉዋን ዢያ ከአል ዐይን ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ የግብርናውን ዘርፍ ለማሻሻል እቅድ መንደፉ የምግብ ዋስትናን በመላው ዓለም ለማረጋገጥ የተሻለ መፍትሄ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል።
ሌላኛው የፋኦ ከፍተኛ ባለሞያ እንደተናገሩት ድርጅቱ የያዛቸውን በርካታ ውጥኖች እና መርሀ-ግብሮች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከምታዘጋጀው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ (ኮፕ 28) በፊት ይቀርባል።
ባለሞያው ለግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ማስተካከያ ማድረግና ዘላቂ የእሴት ሰንሰለቶችን ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።
በዓለም ዙሪያ ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት ፣ የግብርና ምርትን መጨመር፣ ረሃብን መዋጋት እና ኑሮን ማሻሻል ፋኦ ከ2022 እስከ 2031 ድረስ የነደፈው እቅድ ነው።