አረብ ኤምሬትስ ኮፕ 28 ጉባዔን ስኬታማ እንደምታደርግ እምነት አለን--የፈረንሳይ ባለስልጣን
"ግብጽ እንደተሳካላት ሁሉ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኮፕ 28 እንደሚሳካላተሰ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ጉባኤ (ኮፕ 28) በሚቀጥለው ህዳር በዱባይ ይካሄዳል
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ጉባኤ (ኮፕ 28) ስኬታማ እንደምታደርግ እምንተ እንዳላቸው የፈረንሳይ ባለስልጣን ለአል ዐይን ኒውስ ተናረዋል።
የፈረንሳዩ ባለስልጣን ሀገራቸው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (ኮፕ 28) ጉባኤ በምታዘጋጅበት ወቅት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን እንደምትደግፍ ተናግረዋል።
በካይሮ የሚገኙት የፈረንሳይ አምባሳደር ማርክ ባሬቲ በፈረንሳይ እና የኮፕ 27 ጉባኤ ካሰናዳችው ግብጽና ቀጣዩን ጉባኤ ከምታዘጋጀው አረብ ኤምሬትስ ጋር ጥሩ ቅንጅት እንዳለ አረጋግጠዋል።
"ግብጽ እንደተሳካላት ሁሉ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኮፕ 28 እንደሚሳካላተሰ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።
የኮፕ 28 ጉባኤ እ.አ.አ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 12 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ይካሄዳል። በጉባኤው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በመገምገም እ.አ.አ. በ2015 በፓሪስ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ በተስማሙት ግቦች መሰረት እንደሚለካ ይጠበቃል።
የፈረንሳዩ አምባሳደር አክለውም "ለእነዚህ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ስኬት በተለይም ከአየር ንብረት ጋር በተያያዙ የባለብዙ ወገን ጉባኤው ላይ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ሁሌም እንጓጓለን" ብለዋል።
ማርክ ፓሬቲ አክለውም “ስኬቱ የ 1.5 ዲግሪ የዓለም ሙቀት መጨመርን ግብ ማስጠበቅ ነው። ይህ ወሳኝ እርምጃ ነው" በማለት አክለዋል።