ለኮፕ 28 ጉባኤ ስኬት የመግባቢያ ስምምነቶች እየተፈረሙ ነው
የአረብ ኤምሬቶች የመቻቻልና የአንድነት ሚንስቴር እና የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል
ሚንስቴሩ የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች በኮፕ 28 እንዲሳተፉ ማስተባበርና ማበረታታት ላይ ይሰራል
ለኮፕ 28 ጉባኤ ስኬት የመግባቢያ ስምምነቶች እየተፈረሙ ነው።
የአረብ ኤምሬቶች የመቻቻልና የአንድነት ሚንስቴር እና የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ የወንድማማችችን ትስስር፣ ለትዕግስትና በጋራ መኖር ለማጠናከር ያለመ ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ለምታዘጋጀው 28ተኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዲኖረው በማሰብ ስምምነቱ ተካሂዷል።
በተጨማሪም ሚንስቴሩ በጉባኤው ላይ የሚስተናገዱ የተለያዩ ኃይማኖቶችን ግንኙነት ለማሳለጥ ነው።
የመግባቢያ ስምምነቱን የትዕግስትና የአንድነት ሚንስትር ሼክ ነህያን ቢን ሙባረክ አል ነህያን እና የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ሱልጣን አል ጃበር በተገኙበት ተፈርሟል።
ስምምነቱ ሼክ ነህያን ቢን ሙባረክ አል ነህያን የብዝሀ ኃይማኖቶች ዳይሬክተርና ቃል አቀባይ መሆናቸውን አመልክቷል።
ሚንስትሩ የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች ለኮፕ 28 እንዲሳተፉና ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ ማስተባበርና ማበረታታት ላይ ይሰራሉ።
ይህም የኃይማኖት አባቶችና መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎችን እንዲደግፉና አስፈላጊነቱን እንዲገነዘቡ ይዘት ማበልጸግን ያካትታል።