የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ከአጋሮች ጋር ውጤታማ የሆነ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፍላጎት ሰንቀዋል
የኮፕ 28 ፕሬዝደንትና የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ በኮፕ 28 ሁሉንም አካላት ማካተት ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል
ዶ/ር ሱልጣን አል-ጀበር አካታችነትን የማረጋገጥ መርህን በጥረቶቹ ዋልታ አድርጎ ያስቀምጣል ሲሉ በአጽንዖት ተናግረዋል
የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት እና የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ዋና ጸሀፊ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢንዱስትሪ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር እና የኮፕ 28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ካለው የአመራር ራዕይ ጋር ተያይዞ ከአጋሮች ጋር ውጤታማ የሆነ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃ ስርዓት ውስጥ ሁሉም ሰው ሙሉ በሙሉ እንዲካተት፤ በዘላቂ ልማት መስክ ተጨባጭ ውጤቶችን ለማስመዝገብ እና የሁሉንም ሀገራት የጋራ ጥቅሞች ለመደገፍ ተመሳሳይ ራዕይ፣ ሀሳቦች እና አቅጣጫዎች ይወሰዳሉ ተብሏል።
- ሱልጣን አል ጃበር ለኮፕ 28 የመሪዎች ጉባኤ ትልቅ እቅድ እንዳላቸው አስታወቁ
- የግሉ ዘርፍ ውጤታማ የአየር ንብረት ፋይናንስን ማቅረብ ይችላል- ሱልጣን አል-ጃብር
ይህ የተባለው የኮፕ 28 ፕሬዝደንት እና የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት በአስተናጋጅ ሀገሯ የስራ አስፈፃሚ ሴክሬታሪያት ሲፈረም ነው።
ይህም የሁለቱም ወገኖች የግልጽነት መርሆዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እና በኮፕ 28 ወቅት የሁሉንም አካላት ማካተትን ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር እና የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ማዕቀፍ ዋና ጸሃፊ ሲሞን ስቲል በአቡ ዳቢ በተካሄደው ስብሰባ ነው።
የአስተናጋጅ ሀገር ስምምነት የፊታችን ህዳር ለሚካሄደው የኮፕ 28 ጉባኤ የህግ ማዕቀፍ ነው።
ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ ሁለቱ ወገኖች የጋራ መግለጫ በማውጣት በጉባኤው ሂደት ውስጥ ማካተት፣ግልጽነት እና መከባበርን የማረጋገጥ መርሆዎችን ተግባራዊ በማድረግ ጥረቶችን ወደ አንድነት ለማምጣትና ለማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
ዶ/ር ሱልጣን አል-ጀበር አካታችነትን የማረጋገጥ መርህን በጥረቶቹ ዋልታ አድርጎ ያስቀምጣል ሲሉ በአጽንዖት ተናግረዋል።