ፖለቲካ
ኮፕ28 ጉባኤ ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ እንዲተባበር ማድረጉ ተገለጸ
የዓለም ነዳጅ ላኪ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ቀዳሚ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል
የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከዛሬ ጀምሮ በአረብ ኢምሬት ይካሄዳል
ኮፕ28 ጉባኤ ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ እንዲተባበር ማድረጉ ተገለጸ።
የቤልጂየም ጠቅላይ ሚንስትር አሌክሳንደር ዲ ክሮ ለአልዐይን እንዳሉት ኮፕ28 የዓለም ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ አንድነት እንዲፈጥሩ አድርጓል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ብራስልስ ቢዝነስ ጉባኤ ላይ በተሳተፉበት ወቅት እንዳሉት "የተባበሩት አረብ ኢምሬት የታዳሽ ሀይልን ለመጠቀም ብዙ ርቀት የሄደች ሀገር ናት" ብለዋል።
የዓለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ነዳጅ ላኪ ሀገራት ታዳሽ ሀይል ወደመጠቀም መግባት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትር አሌክሳንደር።
አውሮፓ በአየር ንብረት ለውጥ እየተጎዱ ካሉ የዓለም ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ጉዳቱን ለመቀነስ የታዳሽ ሀይል ልማት በማስፋፋት ላይ እንዳሉም ተናግረዋል።
ለአውሮፓዊያን ሀይድሮጅን እንደ ተተኪ የሀይል አማራጭ ለማድረግ አውሮፓ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሆነም ተገልጿል።
በአውሮፓ የኢንዱስትሪዎች መቀነስ የአየር ንብረት ለውጥን አይቀንስም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ የተሻለው መፍትሄ ኢንዱስትሪን እና የአየር ንብረት ለውጥን ማመጣጠን እንደሆነም ገልጸዋል።