በፎረሙ የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር ተገኝተዋል
ከ350 በላይ መሪዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ዱባይ በተካሄደው የኮፕ 28 መዳረሻ ፎረም ላይ ተሳትፈዋል።
ፎረሙ የተዘጋጀው በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ ከሚገኙ 27 የወጣት ድርጅት ቅርንጫፎች ጋር ትብብር ነው።
እንደ ኢምሬትስ የዜና አገልግሎት (ዋም) ዘገባ ከሆነ ፎረሙ ጥረቶችን ለማነቃቃት፣ የጋራ ተግባራትን እና የቀጣናው የግል ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ያለመ ነው።
- በካይ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት ለመለገስ ቃል የገቡትን 100 ቢሊየን ዶላር ሊሰጡ ይገባል - አል ጃበር
- የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት የፓሪሱን ስምምነት ለማሳካት የበለጠ ጥረት ያስፈልጋል አሉ
በፎረሙ የኢንዱስትሪ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር እና የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር ተገኝተዋል።
ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን መዘዝ ለመጋፈጥ በመንግስታት እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
ስርዓትን የተከተለ፣ ኃላፊነት የተሞላበት፣ ፍትኃዊ የኃይል ሽግግርን ለማምጣት ከግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንቱ ተስማሚ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በንግዱ ዘርፍ፣ በመንግስት እና በሲቪል ማህበረሰብ መካከል አጋርነት የመገንባት አስፈላጊነት ነው ብለዋል።
የፎረሙ አካል የሆነው የአየር ንብረት ፎረም ለንግድ እና በጎ አድራጎት ድርጅት በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 1 እና 2 ለማካሄድ ውጥን ተይዟል።