የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት የፓሪሱን ስምምነት ለማሳካት የበለጠ ጥረት ያስፈልጋል አሉ
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር በቻይና በተካሄደው የአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ ደረጃ ፎረም ተሳትፈዋል
የሰው ልጅን እና ምድርን ለመጠበቅ ተጨባጭ የአየር ንብረት እርምጃዎችን እንደሚያረጋግጥ አጽንዖኦት ሰጥተዋል
የአረብ ኤምሬቶች የኢንደስትሪ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር እንዲሁም የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር ትብብርን ማጠናከር ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አመራር ራዕይ መሰረት ጉባኤው ከስልታዊ አጋሮች እና ከሁሉም አካላት ጋር ትብብርን ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።
- የአየር ንብረት ግቦችን በአስቸኳይ ለማሳካት 4.5 ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር
- ኮፕ 28 ጉባኤ ምኞቶችን ወደ ተግባራዊነት የሚለውጥ ተግባራዊ ኮንፈረንስ ይሆናል- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር
ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገትን የሚያስጠብቀው ይህ ትብብር፤ የሰው ልጅን እና ምድርን ለመጠበቅ ተጨባጭ የአየር ንብረት እርምጃዎችን እንደሚያረጋግጥ አጽንዖኦት ሰጥተዋል።
የኤምሬትስ የዜና አገልግሎት (ዋም) እንደዘገበው በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ በተካሄደው የአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ ደረጃ ፎረም፤ አል ጃበር የቻይናን ቀዳሚ ሚና እና በቤልት እና ሮድ ሀገራት እና በመላው ዓለም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመደገፍ የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል።
የፓሪሱን ስምምነት ዓላማዎች የማሳካት እድልን ለማስጠበቅ ዓለም የበለጠ ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልገውም የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ጠቁመዋል።
በተጨማሪም በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራና ጥልቅ መሆኑን ገልጸው፤ በመከባበር፣ በወዳጅነት እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል።