ፖለቲካ
ለዩክሬን ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሀገራት እነማን ናቸው?
የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ 41 የሚጠጉ ሀገራት ለኬቭ የፋይናንስ፣ ወታደራዊ እና ሰብአዊ ድጋፍ አድርገዋል
ምዕራባዊያን የ380 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን 118 ቢሊየኑ ወታደራዊ ድጋፍ ነው
የሩስያ እና ዬክሬን ጦርነት የአለምን ፖለቲካዊ አሰላለፍ ቅርጽ በብዙ የቀየረ እንደሆነ ይነገርለታል።
ምዕራባዊያን በጦርነቱ ከዩክሬን ጋር ወግነው ሩስያን ሲዋጉ ሞስኮ በበኩሏ ከጥቂት ደጋፊዎቿ ጋር ሆና ዘልቃለች፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረበት የካቲት 24 2022 አንስቶ እስካሁን ድረስ 41 የሚደርሱ የአለም ሀገራት ለዩክሬን የሰብአዊ፣ የፋይናንስ እና ወታደራዊ ድጋፎችን ሲያደርጉ አሜሪካ እስካሁን 51 ቢልዮን ዶላር ግምት ያላቸውን ጦር መሳርያዎችን ለኬቭ በመስጠት በወታደራዊ ድጋፍ ቀዳሚዋ ናት፡፡
ከዚህ ባለፈም በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተፈርሞ ምክር ቤቱ እንዲዘገይ ባደረገው የ95 ቢልዮን ዶላር የውጭ ሀገራት እርዳታ ረቂቅ ውስጥ ለዩክሬን 61 ቢልዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ መድባለች፡፡
የአውሮፓ ሀገራት እና ድርጅቶች፣ ቡድን 7፣ ቻይና፣ ቱርክ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ህንድ፣ አውስትራሊያ እና ኖርዌይ ድጋፍ ካደረጉ 41 ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ለዩክሬን ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ ሀገራት የትኞቹ ናቸው የሚለውን ከስር ካለው ምስል ይመልከቱ፤ ድጋፉ ከየካቲት 2022 እስከ ጥር 15 2024 የተደረገውን የሚያጠቃልል ነው።