ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ኔቶ የሩሲያን ሚሳኤል መቶ እንዲጥል ጠየቁ
የኔቶ አባል ሀገራት በራሳቸው የአየር ክልል ሆነው የሩሲያን ሚሳኤል ቢመቱ ምንም ችግር አያመጣባችሁም ብለዋል
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀገራቱ ባሉበት ሆነው በዩክሬን ሰማይ ላይ የሚገቡ የሩሲያን ሚሳኤል ምቱልን ሲሉ ጠይቀዋል
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የኔቶ አባል ሀገራት የሩሲያን ሚሳኤል እንዲመቱ ጠየቁ።
ከሩሲያ ጋር እየተዋጉ ያሉት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጎረቤት የሆኑ የኔቶ አባል ሀገራት እንዲያግዙ ጠይቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከኒዮርክ ታየምስ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ሉዩክሬን ጎረቤት የሆኑ ሀገራት ከግዛታቸው ሆነው የሩሲያን ሚሳኤል መምታት ይችላሉ ብለዋል።
"የኔቶ አባል ሀገራት ወደ ዩክሬን ግዛት የገቡ የሩሲያን ሚሳኤል መምታት ይችላሉ ፣ ይህን ማድረግ በሩሲያ ላይ ጥቃት መሰንዘር አይደለም" ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
የኔቶ አባል ሀገራት ሩሲያ በዩክሬን ሙሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ውድመቶችን ለመከላከል ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።
ጀርመን፣ ፖላንድ እና የተወሰኑ የኔቶ አባል ሀገራት ዩክሬንን ከሩሲያ ሚሳኤል እንዴት እንደሚጠብቁ ከተወያዩ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ኔቶ በበኩል የዩክሬን ጎረቤት የሆኑ አባል ሀገራትን ከሩሲያ ሚሳኤል እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል በመምከር ላይ መሆኑን ከዚህ በፊት ሙግለጹ ይታወሳል።
ሞስኮ በበኩሏ ከኔቶ ጋር የቀጥታ ጦርነት ለመጀመር በቂ ምክንያት እንዳላት እና ይህም ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል አስጠንቃለች።