የኢድ-አል አድሃ በዓልን ሳኡዲ አረቢያ ከምታከብርበት ቀን ውጭ የሚያከብሩ ሀገራት
ኢድ አል አድሃ በእስልም እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩት ሁለት ዋና በዓላት አንዱ ነው
ሞሮኮ፣ኢንዶንኤዥያ፣ማሌዥያ፣ጃፖን፣ሲንጋፖር እና ቡሩንዲ ሳኡዲ በምታከብርበት ቀን አያከብሩም
ኢድ አል አድሃ በእስልም እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩት ሁለት ዋና ባዓላት አንዱ ነው። ሌላኛው ትልቅ በዓል ኢድ አልፈጥር ነው።
ሳኡዲ አረቢያ ኢድ አል አድሃ ወይም አረፋን በፈረንጆቹ ሰኔ 28 እንደምታከብር የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።
ሞሮኮ፣ኢንዶንኤዥያ፣ማሌዥያ፣ጃፖን፣ሲንጋፖር እና ቡሩንዲ ሳኡዲ በምታከብርበት ቀን አያከብሩም።
የዘንድሮ ሀጅ በኮሮና ወረርሽኝ ምከንያት በተሳታፋዎች ቁጥር ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ሙሉ በሙሉ ከተነሳ በኋላ የሚከበር ነው።
በዓለም ደረጃ የኮሮና ወረረሽኝ ተከስቶ የነበረበት ወቅች፣ በሀጅ ተጓዦች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ይታወሳል።
በኮሮና ወቅት ሳኡዲ አረቢያ ትንሽ ቁጥር ያለው ምዕመን ተራርቆ እንዲያከብር የሚያስገድድ ህግም አውጥታ ነበር።
በዘንድሮ ሀጅ ለሀጅ ተጓዦች መመላሻ የሚሆን 1000 ባሶችን አዘጋጅታለች።
ለተጓዞች የአገልግሎች ክፍያ ቅናሽም ተደርጓል።
በዘንድሮው ሀጅ 2.6 ሚሊዮን ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።