ሮቦቱ በአንድ ጊዜ ሶስት አይት ምግቦችንና ሾርባዎችን ማዘጋጀት ይችላል
የቻይናው ዛዮሚ የቴክኖሎጂ ኩባያ የሼፎችን ስራ ይጋፋል የተባለ ምግብ አብሳይ (ሼፍ) ሮቦት ከሰሞኑ አስተዋውቋል።
ዛዮሚ አዲስ ይዞት የመጣው ምግብ አብሳይ ሮቦት 35 አይነት ስራዎችን መስራት የሚችል እንደሆነም መረጃዎች ይጠቆማሉ።
የቻይናው ዛዮሚ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከሆነ አዲሱ ምግብ አብሳይ ሮቦት መክተፍ፣ መፍጨት፣ ጭማቂ መስራት እና በእንፋሎት ማብሰልን ጨመሮ በርካታ ስራዎችን መከወን የሚችል ነው።
አዲሱ ስማርት ምግብ አብሳይ ሮቦት በአንድ ጊዜ ለሶስት ሰው የሚበበቃ ወይም ሶስት ሰሃን ምግብ እና ሾርባ መሰመስራት የሚችል መሆኑንም ኩባንያው አስታውቋል።
በካምብሪጅ ተመራማሪዎች የተሰራው ሮቦቱ መጀመሪያ ላይ እንቁላል በቲማቲም እንዲሰራ ተደርጎ ሙከራ እንደተረገበትም ተነግሯል።
ሮቦቱ በምግቡ ውስጥ ያለውን የጨው መጠን የሚለይበት ሴንሰር የተገጠመለት መሆኑንም ዛዮሚ ኩባንያ አስታውቋል።