ጦርነቱ መቀጠሉ ለዩክሬን መልሶ ግንባታ የሚያስፈልገው ገንዘብ በየጊዜው እየጨመረ እንደሆነ ተገልጿል
በለንደን የተካሄደው ለዩክሬን የመልሶ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 60 ቢሊዮን ዶላር ሰበሰበ።
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ላለችው ዩክሬን በብሪታንያ አስተባባሪነት ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በለንደን ለኩለት ቀናት በተካሄደው በዚህ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ 56 ሀገራት ተሳትፈዋል ተብሏል።
ከሩሲያ በሚተኮሱ የጦር መሳሪዎች ዋና ዋና መሰረተ ልማቷ የወደመባት ዩክሬን የጦር መሳሪያ በማሰባሰብ ላይ ትገኛለች ።
የዓለም ባንክ ከአንድ ዓመት በፊት ባወጣው ሪፖርት መሰረት ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት ከ400 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል።
የአውሮፓ ህብረት፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ ከፍተኛ ገንዘብ ለዩክሬን ካዋጡ ሀገራት እና ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ሀገራቱ ለዩክሬን ለመለገስ ቃል የገቡትን ገንዘብ እስከ ሶስት ዓመት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ለዩክሬን እንደሚያስተላልፉ አስታውቀዋል።