ለእስራኤል የጦር መሳሪያ አቅርቦትን እንደሚያቆሙ ያሳወቁ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ሀገራት ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ሽያጭ እንዲያቆሙ የሚደረጉ አለም አቀፍ ጥሪዎች እየጨመሩ መጥተዋል
በጋዛ በሲቪል ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ ሲሆን፤ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ28 ሺህ ተሻግሯል
በጋዛ በሲቪል ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ መምጣቱን ሀገራት ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ሽያጭ እንዲያቆሙ የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጥሪዎች እየተበረከቱ መጥተዋል።
አራት ወራን ባስቆጠረው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ28 ሺህ ያለፈ ሲሆን፤ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎም ለእስራኤል ወታደራዊ ድጋፍ ያደርጋሉ በተባሉት ሀገራት ላይ ጫናዎችና ውግዘቶች እየተበራከቱ መጥተዋል።
ለእስራኤል መሳሪያ የሚያቀርበው ማነው?
በፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2022 ድረስ ባው ጊዜ 68 በመቶው የእስራኤል የጦር መሳሪያዎች ከአሜሪካ የመጡ መሆናቸውን የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት የጦር መሳሪያ ዝውውሮች ዳታቤዝ መረጃ ያመለክታል።
የአሜሪካ መከላከያ በእስራኤል ውስጥ ለራ የሚጠቀምባቸውን የጦር መሳሪያዎች ማከማቻ መጋዘን ያለው ሲሆን፤ አሜሪካ በጋዛ ጦርነት ወቅት እስራኤል ከእነዚህ መሳሪያዎች መካከል አንዳንዶቹን እንድትጠቀም ፈቅዳለች።
ከአሜሪካ በመቀጥልም 28 በመቶ የእስራኤል ጦር የታጠቃቸው ጦር መሳሪያዎችን ከጀርመን የምታገኝ ሲሆን፤ የጀርን ጦር መሳሪያ የወጪ ንግድ በ2023 በ10 እጥፍ መጨመሩም ነው የተገለጸው።
ብሪታኒያም ሌላኛዋ ለእስራኤል ጦር መሳሪያ አቅራቢ ሀገር ስትሆን፤ ከፈረንጆቹ 2015 ወዲህ 549 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ጦር መሳሪያዎችን ለእስራኤል አቅርባለች።
ካናዳ፣ አውስትራሊያ እና ፈረንሳይም ለእስራኤል በከፍተኛ ደረጃ የጦር መሳሪያ ከሚያቀርቡት ውስጥ ሲሆን፤ አቅርቦታቸውን እንዲያቆሙም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው ይገኛል።
ለእስራኤል የጦር መሳሪያ አቅርቦትን እንደሚያቆሙ ያሳወቁ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ኔዘርላንድስ፤ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት የኔዘርላንድስ መንግስት የኤፍ-35 ተዋጊ ጄት አካላትን ለእስራኤል መላ እንዲያቆም የአንድ ዓመት ጊዜ ሰጥቷል። የሀገሪቱ ፍርድ ቤት የኤፍ-35 ተዋጊ ጄት አካላትን መላክ ዓለም አቀፍ ህጎች መጣስ ነው ሲልም አስታውቋል።
ቤልጂየም፤ በቤልጂየም አንድ የክልል መንግስት ወደ እስራኤል የጦር መሳሪያዎች የሚልኩ የሁለት ኩባያዎች ፈቃዶችን ማገዱን ተናግሯል። ክልላዊ መንግስቱ እግዱን ያሳለፈው የዓለም የፍትህ ፍርድ ቤት እስራኤል የዘር ማጥፋት ከመፈጸም እንድትቆጠብ ማሳሰቡብ ተከትሎ እንደሆነ ነው።
ጃፓን፤ የጃፓኑ ኢቶቹ ኮርፖሬሽን ባሳለፍነው ሳምንት ከእስራኤሉ የመሳሪያ አምራች ኩባንያ ኤልቢት ጋር ያለውን የመሳሪያ አቅርቡት ስምምነት መቀያየሩን አስታውቋል።
ኩባያው ውሉን ያቋረጠው ከጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መሆኑን እና ውሉ የተቋረጠው የዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ውሳኔን በማክበር እንደሆነም አስታውቋል።
ጣሊያን፤ የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ እንዳስታወቁት ጣሊያን ከፈረንጆቹ ጥር 20 ጀምሮ ለእስራኤል የምታደረገውን ሁሉንም አይነት የጦር መሳሪያ አቅርቦት አቋርጣለች ብለዋል።
ስፔን፤ የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራው ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለእስራኤል ምንም አይነት ጦረ መሳሪያ ሸጣ እንደማታውቅ ገልጸዋል። ሆኖም ግን የስፔኑ ኤል ዴሪዮ ጋዜጣ ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ ባሳለፍነው ህዳር ወር ብቻ ስፔን 1.1 ሚሊየን ዋጋ ያላቸው ጥይቶችን ለእስራኤል አቅርባለች ብሏል።