አንድ ገንዘብ ደካማ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
አንድ ገንዘብ ደካማ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
የአንድ ሀገር ገንዘብ በሌላ ሀገር ገንዘብ ሲመነዘር ዋጋው ከቀነሰ ገንዘቡ ደካማ ሆኗል ማለት ነው።
ብዙን ጊዜ ደካማ ገንዘብ ያላቸው ሀገራት በደሃ የኢኮኖሚ መሰረት ወይም ስርአት ወስጥ ያሉ ሀገራት ናቸው።
ነገርግን ገንዘባቸው ደካማ የሆነ ሀገራት ሁሉ ደሃ ሀገራት ናቸው ብሎ መደምደም አይቻልም።
ገንዘብን ማዳከም የራሱ ጥቅም አለው። አንዳንድ ጊዜ ሀገራት ገንዘባቸውን በማዳከም የመግዛት አቅሙ እንዲቀንስ ያደርጋሉ። ሀገራት ይህን ፖሊሲ የሚከተሉት ወደ ውጭ መላክን ለማበረታት እና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ለመቀነስ በማለም ነው።
በዶላር ሲመነዘር ቁጥር አንድ ደካማ የሆነው የኢራን ሪያል ነው። አንድ ዶላር በ42,300 የኢራን ሪያል ይመነዘራል።
ቁጥር ሁለት ደካማ ገንዘብ የቬትናሜዝ ዶንግ ሲሆን አንድ ዶላር በ23,485 ዶንግ ይመነዘራል።