ብራዚል እና ቻይና ከዶላር ውጪ በሆነ ገንዘብ ለመገበያየት ተስማሙ
ሁለቱ ባለብዙ ኢኮኖሚ ባለቤቶች በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት አዲስ ስምምነት ተፈራርመዋል
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ የዓለማችን ሀገራት ከዶላር ውጪ ባሉ ገንዘቦች ለመገበያየት ስምምነቶችን በመፈራረም ላይ ናቸው
ብራዚል እና ቻይና ከዶላር ውጪ ዘሆነ ገንዘብ ለመገበያየት ተስማሙ።
ቻይና ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት ወደ መካረር ማምራቱን ተከትሎ ከዚህ በፊት በአሜሪካ ዶላር ስታደርጋቸው የነበሩ የንግድ ልውውጦችን በመቀየር ላይ ትገኛለች።
ቤጂንግ ከዚህ በፊት ከሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ጋር የመገበያያ ገንዘቧን በዩዋን እና ከዶላር ውጭ እንዲሆን አድርጋለች።
አሁን ደግሞ ከላቲን አሜሪካዋ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ከሆነችው ብራዚል ጋር ዶላርን ላለመጠቀም ተስማምታለች ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።
የብራዚሊያ እና ቤጂንግ አዲስ የንግድ ስምምነት ዶላርን በመተው በየራሳቸው ገንዘቦች ለመጠቀም ተስማምተዋል ተብሏል።
የቻይና እና ብራዚል ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ ከ150 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደደረሰ ተጠቅሷል።
ሁለቱ የብሪክስ መስራች ሀገራት በተለይም አዲሱ ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ በምርጫ ማሸነፋቸው ለሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻሻል አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።
ሩሲያ ከቀጣዩ ክረምት ወራት ላይ ከሚካሄደው አፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ በኋላ የንግድ ግንኙነቷን ከዶላር ውጪ እንደምታደርግ ይጠበቃል።
ብዙ የዓለማችን ሀገራት በውጭ ምንዛሬ እጥረት እየተፈተኑ ሲሆን ከዶላር ውጪ የሚደረጉ የንግድ ልውውጦችን ብዙ ሀገራት እንደሚመርጡት ይጠበቃል።
ጎረቤት ሀገር ኬንያ በዶላር እጥረት ምክንያት ከሳውዲ አረቢያ ጋር የነዳጅ ግብይቷን በሽልንግ ለማድረግ መስማማቷን አስታውቃለች።