ሲጋራ በብዛት የሚጨስባቸው 10 ሀገራት
በዓለማችን 1 ነጥብ 25 ቢሊዮን ህዝብ ትምባሆ ተጠቃሚ መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ
ሰርቢያ፣ ቡልጋሪያ እና ክሮሽያ ከጠቅላላ ህዝባቸው ውስጥ ከ33 በመቶ በላዩ ሲጋራ ይጨሳሉ
የመተንፈሻ አካላትን ጨምሮ ለበርካታ ህመሞች ምክንያት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ጥናቶች ያስረዳሉ።
በዓለማችን ላይ 1 ነጥብ 25 ቢሊዮን ህዝብ ትምባሆ ተጠቃሚ ሲሆን የአጫሾች ቁጥር አንድ ጊዜ ቅናሽ አሳይቶ ነበር።
በ2000 ላይ በተደረገ ጥናት በመላው የዓለማችን ሀገራት በተወሰደ ናሙና ከ5ቱ ሰዎች አንዱ ሲጋራ ያጨስ ነበር።
በ2022 በተደረገ ተመሳሳይ ጥናት ከ3ቱ ሰዎች አንድ ሰው ብቻ ሲጋር እንደሚያጨስ መመላከቱ የሚታወስ ነው።
አሁን ላይ የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸሩ ከፍተኛ አጫሾች የሚገኙባቸው ናቸው ተብሏል።
በተለይም በሰርቢያ፣ ቡልጋሪያ እና ክሮሽያ ከ33 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሲጋራ ያጨሳል ተብሏል።