የትዳር ፍቺ የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኛቹ ናቸው?
ማልዴቪስ ካዛኪስታን እና ሩሲያ ከፍተኛ የትዳር ፍቺ መጠን ካለባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
በስሪላንካ እና ቬትናም ጥንዶች እንዲጋቡ መንገዶች ቀላል ሲሆኑ ፍቺ ለመፈጸም ግን መስፈርቶቹ ብዙ ናቸው
ትዳር መመስረት የሰዎች ፍላጎት እና ምርጫ ሲሆን መተሳሰብ ፣ ፍቅር እና ልጆችን መውለድ ደግሞ ከትዳር የሚገኙ በረከቶች ናቸው፡፡
አብዛኛው ዓለማችን ማህበረሰብ ለትዳር አወንታዊ አመለካከት ያላቸው ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ደግሞ ትዳር ሊፈርስ ይችላል፡፡
እንደ ፎርብስ መጽሄት ጥናት ከሆነ የኮሮና ቫይረስ መከሰት በትዳር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖፈጥሯል፡፡
ከ2020 ጀምሮ በዓለማችን ላይ የሚጋቡ እና የሚፋቱ ባለ ትዳሮች ቁጥር እንደቀነሰ ይሄው ጥናት ያስረዳል፡፡
ከሰሞኑ በወጣ ተጨማሪ ጥናት ደግሞ በተለያዩ ሀገራት ከሚጋቡ 1 ሺህ ጥንዶች መካከል በማልዴቪስ 6 በመቶ፣ በካዛኪስታን 5 በመቶ እንዲሁም በሩሲያ 4 ነጥብ 4 በመቶ ያህሉ ይፋታሉ፡፡
ለፍቺ ዋነኛ ምክንያት የተባሉት ሀላፊነትን አለመወጣት፣ አለመታመን፣ የአመለካከት አለመጣጣም እና ድህነት ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በስሪላንካ እና ቬትናም ጥንዶች እንዲጋቡ መንገዶች ቀላል ሲሆኑ ፍቺ ለመፈጸም ግን መስፈርቶቹ ብዙ ናቸው ተብሏል፡፡