ዩክሬን ኤፍ 16 ጄቶችን ከሌሎች ሀገራት እንድታገኝ ፕሬዝዳንት ባይደን ፈቅደዋል
የአሜሪካው ሎክሄድ ማርቲን ኩባንያ ከፈረንጆቹ 1970 ጀምሮ ኤፍ 16 የጦር ጄት እያመረተ ነው።
እስካሁንም 25 ሀገራት ጄቱን ገዝተው ይጠቀሙበታል።
ዩክሬንም ከሩሲያ ጋር ለምታካሂደው ጦርነት የጦር ጄቱን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥያቄ ስታቀርብ ቆይታለች።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም በቅርቡ ኤፍ 16 ጄት ያላቸው ሀገራት ለኬቭ ጄቱን መስጠት እንደሚችሉ መፍቀዳቸው የሚታወስ ነው።
ይህም ከጦርነቱ በፊት ከነበራት 100 የጦር አውሮፕላን 60ዎቹ የወደሙባትን ዩክሬን የአየር ሃይል ለማጠናከር እንደሚያግዝ ታምኖበታል።
በርካታ ኤፍ 16 የጦር ጄት ያላቸውን 10 ሀገራት ዝርዝር ይመልከቱ፦