በ2020 ለገበያ የቀረበው የወርቅ ማዕድን ምርት 3 ሺህ 478 ቶን ነው
ወርቅ በዓለም ላይ ካሉ የከበሩ ማዕድን አንዱ ነው።
የአለም የወርቅ ጉባኤ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በ2020 ለገበያ የቀረበው የወርቅ ማዕድን ምርት 3 ሺህ 478 ቶን ሲሆን፤ ይህም ለሁለተኛው ተከታታይ ዓመት ቀንሷል።
ቻይና ከፍተኛ የወርቅ አምራች እና ተጠቃሚ ናት። ሀገሪቱ 368.3 ቶን በማምረት 11 በመቶውን የዓለም የማዕድን ምርት ትይዛለች።
በየዓመቱ ምን ያህል ወርቅ እየቆፈረ ነው? የትኞቹ ሀገራትስ በቀዳሚነት ያመርታሉ?