ፖለቲካ
ብዙ መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ደቡብ አሜሪካ፣ አፍሪካ እና እስያ ብዙ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት የተካሄደባቸው አህጉራት ተብለዋል
ከአፍሪካ ቤኒን፣ ናይጀሪያ እና ቡርኪናፋሶ ብዙ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት ያስተናገዱ ሀገራት ናቸው
መፈንቅለ መንግሥት በህዝብ ተመርጦ ስልጣን በተቆጣጠረ አካል ላይ ስልጣን ለመያዝ አልያም ለመቆጣጠር ሀይልን በመጠቀም የሚደረግ ተግባር ነው።
ከፈረንጆቹ 1945 እስከ 2022 ድረስ ባሉት 78 ዓመታት ውስጥ በ10 ሀገራት ውስጥ ብቻ ከ120 ጊዜ በላይ መፈንቅለ መንግሥት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተፈጽሟል።
ደቡብ አሜሪካ፣ አፍሪካ እና እስያ ደግሞ በአንጻራዊነት በተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግሥት የተፈጸመባቸው አህጉራት ናቸው።
ቦሊቪያ፣ አርጀንቲና እና ፓራጓይ ከደቡብ አሜሪካ አህጉር ብዙ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት የተፈጸመባቸው ሀገራት ተብለዋል።
እንደ ስታስቲካ መረጃ ኮነ ከአፍሪካ ቤኒን፣ ናይጀሪያ እና ቡርኪናፋሶ ብዙ ጊዜ መፈንቅለ መንግሥት ያስተናገዱ ሀገራት ናቸው።