በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ያላቸው ሀገራት
3 ሺህ 88 ከ150 ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ህንጻዎች ባለቤቷ ቻይና በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችን በመገንባት ቀዳሚ ናት
828 ሜትር ቁመት ያለው የዱባዩ ቡርጀ ከሊፋ የአለማችን ቁጥር 1 ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ክብረወሰንን እንደያዘ ነው
ረጃጅም ህንጻዎችን መገንባት የዘመናዊ ከተሞች መገለጫ ነው።
በ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻና በ20ኛው ክፍለዘመን መግቢያ ባለ10 ፎቅ ህንጻዎች ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር።
አሁን ላይ ግን ከ100 ሜትር በላይ ቁመት የሌላቸው ህንጻዎች ሰማይ ጠቀስ የሚለው ቅጽል አይሰጣቸውም።
ከ40 እስከ 163 ለመኖሪያ እና ለንግድ ግልጋሎት የሚውሉ ፎቆች ያሏቸው ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎች ከዱባይ እስከ ሻንጋይ በብዛት ተገንብተዋል።
ከ150 ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው 3 ሺህ 88 ህንጻዎች ባለቤት የሆነችው ቻይና በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችን በመገንባት ቀዳሚዋ ሀገር ናት፤ 632 ሜትር ቁመት ያለው የሻንጋይ ታወርም የአለማችን ሶስተኛው ረጅም ህንጻ ነው።
ከ345 በላይ ከ150 ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ህንጻዎችን የገነባችው አረብ ኤምሬትስ ደግሞ የአለማችን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ባለቤት ናት፤ 828 ሜትር ቁመትና 163 ፎቆች ያሉት ቡርጀ ከሊፋ መገኛው ዱባይ ነው።
878 ከ150 ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ህንጻዎች ባለቤት የሆነችው አሜሪካም በሰማይ ጠቀስ ህንጻ ግንባታ ከቀዳሚዎቹ ውስጥ ትመደባለች።
ከ300 ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችን በመገንባት ቀዳሚ የሆኑ ሀገራትን ዝርዝር ይመልከቱ፦