ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ አሁናዊ መረጃ
ወረርሽኙ በኢትዮጵያ 7 ሺህ 600 የሚሆኑ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል
የኮቪድ 19 አዲስ ዝርያ ሊመጣ ስለሚችል የመከላከል ጥረቴ ይቀጥላል ብሏል የጤና ሚኒስቴር
የዓለም የጤና ድርጅት ከሦስት ዓመታት በኋላ ኮቪድ-19 የዓለም የጤና አደጋነቱ ማብቃቱን ባለፈው ሳምንት አውጇል።
የኢትዮጵያ ጤና ሚንስቴር በበኩሉ አዲስ ዝርያ ሊመጣ ስለሚችል የመከላከል ጥረቴ አያበቃም ብሏል።
በሀገሪቱ ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የላብራቶሪ ምርመራዎች ተደርገው፤ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።
7 ሺህ 600 የሚሆኑ ሰዎችም በወረርሽኙ ህይወታቸው ማለፉን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኮቪድ 19 በኢትዮጵያ ያለበትን አሁናዊ ገጽታ ይመልከቱ፦