“በስሙ ምክንያት እንደኔ የተሰቃየ የለም” - ኮሮና
አሜሪካዊቷ ኮሮና ማክኪይ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊትም ሆነ በኋላ “ልዩ ስሜን ስትናገር የሚያምነኝ የለም” ይላሉ
በተለይ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ በርካታ ችግሮችን ያሳለፉት ኮሮና፥ “ስሜን ትርጉሙን ባላውቀውም ልቀይረው አልፈልግም” ብለዋል
የተለየ ስም ያላቸው ሰዎች ከአካባቢያቸው ራቅ ሲሉ መልከ ብዙ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋል።
አሜሪካዊቷ የ66 አመት አዛውንት ግን “እንደኔ በስሙ ምክንያት የተቸገረ የለም” ባይ ናቸው።
አዛውንቷ ከ66 አመት በፊት በወላጆቿ የወጣላቸው ስም ኮሮና ማክኪይ የሚል ነው።
ተወልደው ባደጉበት ፒንሲልቫኒያ ስማቸውን የሚጋራ ባለመኖሩ ኮሮና ተብሎ ሲጠራ ያለምንም ማመንታት አቤት እንደሚሉ የሚናገሩት ኮሮና ማክኪይ፥ “ትርጉሙ ባይገባኝም ማንነቴ ስለሆነ ስሜን እወደዋለሁ” ይላሉ።
ልዩ ስማቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ለበርካቶች ግልጽ አለመሆኑ ደጋግሞ ለማስረዳትና ፊደላቱንም በቅደመ ተከተል ለመናገር አስገድዷቸዋል።
በአንድ ወቅት ወደ ሜክሲኮ ለጉብኝት ሲያቀኑም፥ ስማቸውን ኮሮና ከተባለው ቢራ ጋር እያገናኙ ሲያፌዙባቸው እንደነበር ይናገራሉ።
ከሶስት አመት በፊት ሰመ ሞክሼ ሆኖ የተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ደግሞ ከአለም የጤና ስጋትነቱ ባሻገር ለአዛውንቷ ተደራራቢ ፈተናን ይዞ መጥቷል።
የልጅ ልጆቻቸው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስያሜ ከአያታቸው ስም ጋር በመመሳሰሉ ኮሮና ብለው ማውራት እስካለመፈለግ ደርሰዋል።
እሳቸውም በየሄዱበት ሁሉ ስማቸው እየተከተላቸው ብዙ ችግር አሳልፈዋል ይላል የሚረር ዘገባ።
“የኮሮና ወረርሽኝ በተቀሰቀሰ ሰሞን ሀኪም ቤት ሄጄ ነበር፤ ነርሶቹ ስሜን አይተው በመጠራጠር ስሜን ጽፌ እንድሰጣቸው ጠየቁኝ፤ ስጽፈው በድንጋጤ ተዋጡ፤ ተራዬ ደርሶ ተጠርቶ ስገባም ሁሉም ነርሶች እጃቸውን አጣጥፈው በአግራሞት ያዩኝ ነበር” ብለዋል ኮሮና።
ከወረርሽኙ ሞክሼ የሆነው ስማቸው ከባንኮችና የጸጥታ ተቋማት ጭምር እየተደወለ በርግጥም “ስምዎ ኮሮና ነው?” የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን አከተትለው እንዲጠይቁ ምክንያት ሆኗል።
ስማቸው በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት በበርካቶች በአይነ ቁራኛ እንዲታዩ ቢያድርጋቸውም የመቀየር ግን ምንም አይነት ሃሳብ እንደሌላቸው ነው ኮሮና ማክኪይ የተናገሩት።