ሲፒጅ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት "ስራቸውን በመስራታቸው የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞችን ያለቅድመሁኔታ" እንዲፈቱ አሳስቧል
ፈረንሳያዊው ጋዜጠኛ ከእስር ተለቆ ወደ ሀገሩ መመለሱን ሲፒጄ አስታወቀ።
ባለፈው ሳምንታት በኢትዮጵያ ታርሮ ነበረው ፈረንሳያዊ ጋዜጠኛ አንቶኒ ጋሊንዶ ትናንት ከእስር ተፈትቶ ወደ ሀገሩ መመሉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች(ሲፒጄ) ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
- ፈረንሳያዊው ጋዜጠኛ ከታጣቂ ቡድኖች ጋር በማሴር ተጠርጥሮ በኢትዮጵያ መታሰሩን ሲፒጄ ገለጸ
- የኢትዮጵያ መንግስት የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ መልቀቅ አለበት-ሲፒጄ
የጋዜጠኛውን መለቀቅ በበጎ መቀበሉን የገለጸው ሲፒጅ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት "ስራቸውን በመስራታቸው የታሰሩ ሌሎች ጋዜጠኞችን ያለቅድመሁኔታ" እንዲፈቱ አሳስቧል።
በጋዜጠኛው ላይ የተፈጸመው "አግባብነት የሌለው እሰር በዛሬዋ ኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ስራ አደጋ ውስጥ መግባቱን የሚያሳይ ነው" ያሉት የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ የጋዜጠኛው መለለቅ "ትልቅ ዜና ነው" ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው ጠቅሷል።
አስተባባሪው አክለውም መንግስት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ታስረው የሚገኙ ሌሎች ጋዜጠኞችን መልቀቅ አለበት ብለዋል።
ሲፒጄ የጋዜጠኛውን መታሰር አስመልክቶ አውጥቶት በነበረው መግለጫው ጋዜጠኛው የታሰረው ህጋዊ እውቅና ያለውን የኦነግ አባል ቤቴ ኡርጌሳን ቃለመጠይቅ በሚያደርግበት ወቅት ነበር።
መቀመጫውን ፓሪስ ላደደረገ 'አፍሪካ ኢንተሊጀንስ ለተባለ' የግል የዜና ድረ ገጽ የሚሰራው ጋዜጠኛው ከቤቴ ጋር መታሰራቸውንም ሲፒጄ መግለጹ ይታወሳል።
ሲፒጄ ጋዜጠኛው የታሰው ስራውን በመስራቱ መሆኑን ገልጾ ያለቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ ጠይቆ ነበር።
ሲፒጄ በዚሁ መግለጫው ጋዜጠኛው መንግስት በሽብርተኝነት ከፈረጀው 'ኦነግ ሸኔ' እና ከመንግስት ጋር እየተዋጉ ካሉት የፋኖ ታጣቂዎች ጋር በማሴር በአዲስ አበባ ሁከት ለማስነሳት በማቀድ ተጠርጥሮ መሆኑን ፍርድቤት በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸለት ከጠበቃው መረዳቱን ገልጾ ነበር።
ነገርግን የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ቀናት በፊት ጋዜጠኛው ፍቃድ የተሰጠው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን እንዲዘግብ ሆና እያለ እሱ ግን በሀገር ውስጥ ጉዳይ ከፍቃድ ውጭ ቃለ መጠይቅ በማድረጉ ነው ብሏል።
ሲፒጄ ከጋዜጠኛው ጋር አብሮ ታስሮ ስለነበረው ቤቴ ኡርጌሳ ሁኔታ ያለው የለም።
ሲፒጄ በቅርቡ ባወጣው አመታዋ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ስምንት ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ውስጥ ሁለተኛ የጋዜጠኞች አሳሪ አድርጓታል።