የኢትዮጵያ መንግስት የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ መልቀቅ አለበት-ሲፒጄ
የአሜሪካ ኢምባሲ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው ያለው የጋዜጠኞች የጅምላ እስር እንደሚያሳስበው ገልጿል
የአማራ ክልል መንግስት እርምጃ እየወሰደ ያለው በክልሉ ሰላም ለማስፈን እና የሚሰነዘር ጥቃትን ለመመከት ነው ብሏል
አለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተማጓች ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (ሲፒጄ) የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ የታሰሩን 11 ጋዜጠኞችና እና የሚዲያ ሰራተኞች በአስቸኳይ መለቀቀቅ አለበት ብሏል፡፡
መንግስት ባለስልጣናት በሚዲያ ባለሙያዎች ላይ የሚያደርጉትን ማስፈራሪት ያስቁም ሲል ጠይቋል ሲፒጄ፡፡
ሲፒጄ የአማራ ክልል መንግስት እያካሄደ ባለው “የህግ ማስከበር ዘመቻ” ከግንቦት 11 ጀምሮ በአማራ ክልል እና በአዲስ አበባ 11 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች መያዛቸውን ባውጣው ሪፖርት ገልጿል፡፡
ሲፒጄ በክልል በህገወጥ እንቅስቃሴ ተጠርጥረው 4500 ሰዎች መያዛቸውን ጠቅሷል፡፡
“የታሰሩት ንብረትነቱ የግል የሆነው የአሻራ የዩቱዩብ አምስት ጋዜጠኞች፣የንስር ኢንተርናሽናል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 4ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች፤የንቃት ሚዲያ መስራች እና ኤዲተር መስከረም አበራ፤የገበያኑ ሚዲያ መስራችና ባለቤት ሰለሞን ሹምየ” መሆናቸውን ሪፖርቱ ዘርዝሯል፡፡
የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ እርምጃው መንግስት ለፕሬስ ነጻነት እና ለዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ክብር እንደሌላው ያሳያል ብለዋል፡፡ ሲፒጄ በአማራ ክልል ተካሂዷል ካለው እስር በተጨማሪ የኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ ጋዜጠኞች ደሱ ዱላ እና ቢቂላ አሜኑ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡
ከህወሓት ሊሰነዘር ይችላል ያለውን ጥቃት ለመመከት የክልሉን የውስጥ ሰላም በማስፈን እንድነትን ማጠናከር ያስፈልጋል ያለው የክልሉ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚቀጥልበት እየገለጸ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የክልሉን ከትናንት በስትያ “በህግ ማስከበር ዘመቻ”ው ከ4500 በላይ ግለሰቦች መያዛቸውን አስታውቀው ነበር፡፡
የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የህግ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ኃላፊው እርምጃ እየተወሰደ ያለው በፋኖ ስም ተደራጅው በህገወጥ ድርጊት በሚሳትፉት ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ካለፍርድ ቤት ትእዛት እስር እየተካደ ነው፤ታሳሪዎች ከአካባቢያቸው ርቀው በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው እንዳይገናኙ እየተደረገ ነው ሲል በተለይም በአማራ ክልል ያለው ሁኔታ ተችቷል፡፡
የአሜሪካ ኢምባሲ ትናንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው ያለው የጋዜጠኞች የጅምላ እርስ እንደሚያሳስበው ገልጿል፡፡