የክሮሺያ ጠቅላይ ሚንስትር ኮፕ 28ን ተምሳሌታዊ ጉባኤ ለማድረግ እየሰራን ነው አሉ
አረብ ኢምሬትስ የምታዘጋጀው ኮፕ 28 አስፈላጊ የአየር ንብረት እርምጃ እንደሚሆን ይጠበቃል
ጠቅላይ ሚንስትሩ የአየር ንብረት ለውጥ በዋናነት አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል ብለዋል
የክሮሺያ ጠቅላይ ሚንስትር አንድሬጅ ፕሌንኮቪች በአረብ ኢምሬትስ የሚሰናዳው "ኮፕ 28" ተጠቃሽ ጉባኤ እንዲሆን የዓለም ማህበረሰብ እንዲሰራ አሳስበዋል።
ፕሌንኮቪች ለአል ዐይን ኒውስ በሰጡት ልዩ መግለጫ "የአየር ንብረት ለውጥ በዋናነት አስቸኳይ ጉዳይ ሆኗል። እኛም በዓለም ዙሪያ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የተመዘገቡትን የሙቀት መጠኖች እየተመለከትን ነው" ብለዋል።
"በአሜሪካ፣ ቻይና ወይም አውሮፓ ይህ የአየር ሙቀት መጨመር አዝማሚያ እየቀጠለ መሆኑን እና በእርግጥ አሳሳቢ መሆኑን እናያለን" ሲሉ አክለዋል።
በዚህ ረገድ የዓለም ሙቀት መጨመርን ተጽዕኖን ለመገደብ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት "ለወደፊቱ አስቸኳይ እና ዓለም አቀፋዊ ጥረት ነው" ያስፈልጋል በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።
"ሁላችንም በአንድ ጀልባ ውስጥ ነን፤ ዓለም የሁላችንም ናት። እናም አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን" ብለዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ጉባኤን አስመልክቶ ፕሌንኮቪች፤ ኮፕ 28 በተያዘለት ጊዜ እንዲካሄድ በዝግጅት ኮሚቴዎች የተደረጉ በርካታ ዝግጅቶችን እና ስብሰባዎችን ትኩረት ሰጥተዋል።
አረብ ኢምሬትስ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 12 ድረስ የሚደረገውንና የዓለም መሪዎች የሚሳተፉበትን ኮፕ 28 ታስተናግዳለች።
ጉባኤው በጣም አስፈላጊ የሆነውን የአየር ንብረት እርምጃ እንደሚሆን ይጠበቃል።