የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር ከስፔን ንጉስ ጋር ተወያዩ
ውይይታው በዚህ አመት መጨረሻ በሚካሄደው የኮፕ 28 እቅዶች፣ ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መክረዋል
የኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ከአራት ወራት በኋላ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ይካሄዳል
የአረብ ኤምሬትስ የኢንዱስትሪ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር እና የኮፕ 28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር ከስፔን ንጉስ ፍሊፕ 6ኛ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም ዶ/ር ሱልጣነው አልጃብር ከአረብ ኢሚሬትስ መሪዎች ለስፔን ንጉስ ፍሊፕ 6ኛ የተላከ መልእክት አድርሰዋል።
በተጨማሪም የዘንድሮው ዓለም አቀፉ የዓየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አልያም ኮፕ28 ዙሪያ መወያየጣቸውም ተነግሯል።
በውይይታቸውም ውይይታው በዚህ አመት መጨረሻ በሚካሄደው የኮፕ 28 እቅዶች፣ ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ መምከራቸው ነው የተዘገበው።
- ሱልጣን አል ጃበር ለኮፕ 28 የመሪዎች ጉባኤ ትልቅ እቅድ እንዳላቸው አስታወቁ
- የግሉ ዘርፍ ውጤታማ የአየር ንብረት ፋይናንስን ማቅረብ ይችላል- ሱልጣን አል-ጃብር
ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር በስፔን ቆይታቸው በሀገሪቱ በተካሄደው የአውሮፓ ሀገራት የኢነርጂና የአካባቢ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ላይ ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር ከስፔ በፈረንጆቹ 2023 መጨረሻ ላይ በሚካሄደው የኮፕ28 እቅዶችና አላማዎች ዙሪያ ከአውሮፓ ሀገራት ሚኒስትሮቹ ጋር ተወያይተዋል።
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር በስብሰባው ላይ መሳተፋቸው ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም በአየር ንብረት ፋይናንስ ጉዳይ ላይ እድገትን ለማምጣት አስፈላጊውን ተነሳሽነት ለመገንባት እንዲሁም የታዳሽ ኃይልን የማምረት አቅምን ለማሳደግ ያለመ ነው።