ሱልጣን አል ጃበር ለኮፕ 28 የመሪዎች ጉባኤ ትልቅ እቅድ እንዳላቸው አስታወቁ
የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት በሰባተኛው የአየር ንብረት እርምጃ የሚንስትሮች ስብሰባ ነው ይህን ያሉት
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ጉባኤ (ኮፕ 28) በሚቀጥለው ህዳር በዱባይ ይካሄዳል
የአረብ ኤምሬትስ የኢንዱስትሪ እና የላቀ ቴክኖሎጂ ሚንስትር እና የኮፕ 28 ጉባኤ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሱልጣን ቢን አህመድ አል ጃበር፤ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለሚካሄደው ጉባኤ ታላቅ እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የኮፕ 28 ፕሬዝዳንት በሰባተኛው የአየር ንብረት እርምጃ የሚንስትሮች ስብሰባ ነው ይህን ያሉት።
ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራስልስ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አመራር ራዕይ እና መመሪያ በመመራት የህይወት ጥበቃን በማስቀመጥ እና ኑሮን በማሻሻል እንደሚሰሩ አሳስበዋል።
የአየር ንብረት እርምጃ ሰዎችን፣ ተፈጥሮን፣ ምግብን፣ ጤናን እና የመቋቋም አቅምን ያማከለ አካሄድ ለመከተል ወጥነዋል።
- የግሉ ዘርፍ ውጤታማ የአየር ንብረት ፋይናንስን ማቅረብ ይችላል- ሱልጣን አል-ጃብር
- በአየር ንብረት ለውጥ ድርድር የሌለው የሙቀት መጨመርን መቀነስ ነው- ዶ/ር ሱልጣን አል ጃብር
አክለውም "በዚህ አቀራረብ እምብርት ላይ ለዓለም አቀፉ አላማ መላመድ ጠቅለል ያለ እና ቆራጥ የሆነ ማዕቀፍ ለመውሰድ እንሞክራለን። ይህ የጉባኤው አጀንዳ አስፈላጊ አካል የተፈጥሮ ስነ-ምህዳሮችን ለመጠበቅ ቅድሚያ ይሰጣል፣ የአየር ንብረት መዘዝ በጣም የተጋለጡ ማህበረሰቦችን ይጠብቃል፣ ለውጥ እና ህይወትን ለማሻሻል በተጨባጭ እና ተግባራዊ መፍትሄዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው" ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት፣ ካናዳ እና ቻይና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮችን ባሰባሰበው ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር መንግስታት፣ የኢንዱስትሪ ዘርፎች እና ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ባህላዊ የአሰራር ዘዴዎችን በመተው ውጤታማ እና ቆራጥ እርምጃዎችን ለመውሰድ ጥረቶችን በአንድ ላይ እንዲያተኩሩ ጠይቀዋል። ይህም የአየር ንብረት ቀውስን ለመቅረፍ መሰረታዊ ልማትን የሚያመጣ ውጤት ላይ መድረስ ያስይላል ብለዋል።
የኮፕ 28 የድርጊት መርሃ ግብር ግልጽ አቅጣጫ እንዳለው እና ዋና ዓላማው ከ1 ነጥብ 5 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ የሚደርሰውን የዓለም ሙቀት መጠን መከላከል የሚቻልበትን እድል ማስጠበቅ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህንንም ለማድረግ የጉባኤው ፕሬዝዳንት ድርድር ላይ መድረስ እንደሚፈልጉ አስረድተዋል።
በአራት ዋና ዋና ምሶሶዎች ላይ የተመሰረተውን የኮፕ 28 እቅድም ተገምግሟል።