የኤለን መስክ ልጅ የአባቷን ስም ለማስቀየር ፍርድ ቤት ቀረበች
ልጅቱ ስሟን መቀየር የፈለገችው ከአባቷ ጋር ያላትን ትስስር ለመለወጥ ስለምትፈልግ ነው ተብሏል
የኤለን መስክ ልጅ በቅርቡ ጾታ መቀየር የሚያስችል ቀዶ ህክምና ተደርጎላታል
የኤለን መስክ ልጅ የአባቷን ስም ለማስቀየር ፍርድ ቤት ቀረበች፡፡ከአለም ቀዳሚ ባለጸጋ የሆነው ኤለን መስክ ልጅ ባለፈው ሚያዝያ ላይ 18 ዓመት የሞላት ሲሆን ከአባቷ ጋር በተያያዘ ያላትን ትስስር መቀየር እንደምትፈልግ ገልጻለች፡፡
የሁለቱም ጾታ ባለቤት የሆነችው እና በቀዶ ጥገና ወደ የሴትነት ጾታ ያገኘችው በቀድሞ ስሟ ዣቪር አሌክሳንደር መስክ ሁሉ ነገሯ ከአባቷ ጋር መተሳሰሩ እንዳላስደሰታት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንስቷ እንዳለችው “ከአባቴ ጋር መኖርም ሆነ ሌላ ማንኛውንም ነገር ከአባቴ ጋር እንዲገናኝ አልፈልግም” ያለች ሲሆን በካሊፎርኒያ ፍርድ ቤት ተገኝታ የአባቷ ስም እንዲቀየር ለፍርድ ቤቱ አመልክታለች ተብሏል፡፡
እንስቷ ለፍርድ ቤቱ ያመለከተችው ማመልከቻ አዲስ የጾታ ፣ስም እና የውልደት ማስረጃ እንዲሰጣት የሚጠይቅ ሲሆን ጾታዋን በቀዶ ጥገና የቀየረችበትን የሕክምና ማስረጃም አብራ ማያያዟ ተገልጿል፡፡
የ18 ዓመቷ የኤለን መስክ ልጅ ጀስቲን ዊልሰን ከተባለች እንስት የተወለደች ሲሆን ባለጸጋው ከልጁ እናት ጋር በፈረንጆቹ 2008 ላይ ፍቺ መጽመዋል፡፡
ትዊተርን በ44 ቢሊዮን ዶላር በመግዛት የባለቤትነት ጥያቄው በሂደት ላይ ያለው ኤለን መስክ ከልጁ ጋር ለምን ይሄንን ያህል ግጭት ውስጥ ሊገባ እንደቻለ ዘገባው ያለቀው ነገር የለም፡፡
የኤለን መስክም ሆነ የድርጅቱ የቴስላ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ አምራች ኩባንያ የሕግ ክፍል ስለ ጉዳዩ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡
ኤለን መስክ ከቀናት በፊት የሪፐብሊካን ፓርቲን እንደሚደግፍ የተናገረ ሲሆን ዜጎች ጾታቸውን መቀየር እንዳይችሉ ህግ ሊወጣ ይገባልም ሲል ተናግሮ ነበር፡፡