በሐዘን የተጠናቀቀው የቁንጅና ውድድር
በብራዚል ልጄ ለምን አንደኛ አልወጣችም በሚል የተቆጣ አባት ዳኞች ላይ ተኩሷል
የቁንጅና ውድድሩን ልጄ ማሸነፍ ነበረባት ያሉት አባት ሽጉጣቸውን አውጥተው ዳኞች ላይ ሊተኩሱ ሲሉ በፖሊስ ተገድለዋል
በሐዘን የተጠናቀቀው የቁንጅና ውድድር
በደቡብ አሜሪካዊቷ ብራዚል ከሰሞኑ አንድ የሴቶች ቁንጅና ውድድር ተካሂዷል።
ብአልታሚራ በተሰኘችው ከተማ የተካሄደው ይህ የቁንጅና ውድድር ከሁለት ሰዓት በኋላ አሸናፊዎች ተለይተዋል።
ልጃቸው በውድድሩ ላይ እንደምታሸንፍ እርግጠኛ የሆኑ አንድ አባት የውድድሩ አሸናፊዎች ይፋ ከተደረገ በኋላ ቁጣቸውን ይናገራሉ።
ለአንደኝነት ሲጠብቋት የነበረችው ልጃቸው አራተኛ እንደወጣች የተነገራቸው እኝህ አባት ቁጣቸውን መቆጣጠር አልቻሉም።
በቁጣ ብቻ ያልቆመው የአባትየው ድርጊት ሽጉጣቸውን አውጥተው ዳኞችን ልጄ ላይ ግፍ ፈጽማችኋል ብለው ያንባርቃሉ።
በስፍራው የነበረው ፖሊስም ሽጉጥ የደቀኑት አባት ከመተኮሳቸው በፊት ያቆስላቸዋል።
ተፈጥሮ የነበረው ሁከት የቆሰሉትን አባት ወደ ሆስፒታል በመውሰድ ቀለል ያለ ቢመስልም ቆይቶ ወደ ለቅሶ ተቀይሯል።
ከፖሊስ በተተኮሰባቸው ጥይት ቆስለው የነበሩት አባት በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።