ብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ከባድ ዝናብና ቅፅባ ጎርፍ ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቆ ነበር
በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ማጋጠመው የጎርፍ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን ክለፍ ከተማ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጎርፉ ከዚህ በፊት በከተማው ከተከሰቱት የጎርፍ አደጋዎች ከፍተኛው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ገዱት የደረሰባቸውን ሰዎች ላማቋቋምና ህክምና እንዲየገኙ ያደርጋል ብለዋል ም/ከንቲባዋ፡፡
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ የደረስውን ጉዳት እንደሚያጣራ ገልጿል፡፡
ምክትል ከንቲባ አዳነች በጎርፉ ምክንያት አደጋው በአስኮ፣ በአደይ አበባ፣ በጀርመን አደባባይና በጎልፍ ክለብ አካባቢዎች መድረሱን እና መንገዶች እንዲሰጉ ምክንያት ሆነ የነበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ሁኔታ እና የአየር ጸባይ ትንበያ ባለሙያ አቶ ታምሩ ከበደ ከሳምንት በፊት ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቀናት ከባድ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ እና ሌሎች አደጋዎች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ ተናግረው ነበር፡፡
ከሁለት ሳምንታ በፊት በአፋር ክልል አውሲ-ረሱ ዞን አሳዒታ ወረዳ አዋሽ ወንዝ ከመጠን በላይ በመሙላቱ ምክንያት በሦስት ቀበሌዎች ላይ የጎርፍ አደጋ መከሰቱ የሚታወስ ነው፡፡
የክልሉ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሀፈት ቤት በአደጋው አንድ መቶ አባዎራዎች መፈናቀላቸውንና በ 50 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት መድረሱን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡
በባለፈው ዓመት ክረምት በአፋር ክልል ከ 31 ሺ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንና 200 ሺ ሰዎች ንብረታቸው መውደሙን ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መግለጹም ይታወሳል፡፡